Kishore Kumar Hits

Endale Woldegiorgis - Medane текст песни

Исполнитель: Endale Woldegiorgis

альбом: Hyaw Minch


መዳኔ መዳኔ መዳኔ እውን ነው መዳኔ
መትረፌ ኦ መትረፌ መትረፌ እውን ነው መትረፌ
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
አሁን እንኳ ብሞት ወዴት እንደምሄድ ጠንቅቄ አውቃለው
ባዳነኝ ጌታ ላይ ያለኝ መተማመን እስከዚህ ድረስ ነው
ለፍፃሜው ተስፋ እንደማይኖረው ሰው አይደለም ኑሮዬ
የደህንነቴ ቀንድ ቤቴ ስገባ እውን ነው መዳኔ
መዳኔ መዳኔ መዳኔ እውን ነው መዳኔ
መትረፌ ኦ መትረፌ መትረፌ እውን ነው መትረፌ
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ስለዚህ ላምልከው ጌታዬን
ብጮህ አይወጣልኝ ብልለት እልል
የመዳኔ ነገር መች ሆኖ ቀላል
ብጮህ አይወጣልኝ ብልለት እልል
የመዳኔ ነገር መች ሆኖ ቀላል
ይሁን ይሁን አሁንም
ይሁን ይሁን አሁንም
(ይሁን) እጥፍ ክብር
(ይሁን) እጥፍ ምስጋና
(ይሁን) እጥፍ ክብር
(ይሁን) እጥፍ ምስጋና
እውነትና ሕይወት መንገድ የሆነው
ስለ ደህንነቴ ራሱን የሰጠው
ጌታ ኢየሱስን ሳስገባ ወደ ልቤ
ከዘላለም ጥፋት ታወቀኝ መዳኔ
ክፉ እላዬ ላይ ከነጫነው ቀንበር
ፈጥኖ ለቆኛል ጌታዬን ስቀበል
መች ነፍሴ ብቻ ስጋዬም ተረፈ
የክብር ዕቃ መጠቀሚያ ሆነ
ብጮህ አይወጣልኝ ብልለት እልል
የመዳኔ ነገር መች ሆኖ ቀላል
ብጮህ አይወጣልኝ ብልለት እልል
የመዳኔ ነገር መች ሆኖ ቀላል
ይሁን ይሁን አሁንም
ይሁን ይሁን አሁንም
(ይሁን) እጥፍ ክብር
(ይሁን) እጥፍ ምስጋና
(ይሁን) እጥፍ ክብር
(ይሁን) እጥፍ ምስጋና

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители