ንፋሱ ቢነፍስ ወጀቡም ቢያጓራ
በበዛው ሰላምህ አለህ ከእኔ ጋራ
ዓለም ብትነዋወጥ ማዕበሉ ቢበዛ
ነፍሴ እርፍ አለች በፍቅርህ ተይዛ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ኅዋላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ኅዋላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
መልህቄ (፬×)
ያዝከኝ እየሱሴ
መልህቄ (፬×)
ያዝከኝ እየሱሴ
የፍቅርህ ሰንሰለት አጥብቆ ይዞኛል
እኔ ቢደክምበት መቼ ይተወኛል
በሞት ታች ወርደህ መልህቄ ያዝከኝ
ልዩ ፍጥረት ቢሆን ሞትም እንዳይለየኝ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ኅዋላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ኅዋላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
መልህቄ (፬×)
ያዝከኝ እየሱሴ
መልህቄ (፬×)
ያዝከኝ እየሱሴ
እንደ ነብስም መልህቅ በሆነ ተስፋ
እርግጥ እና ፅኑ መቼም የማይጠፋ
በዝህኛው ቢሆን በወደኛው ዓለም
ጥብቅ አርገህ ያዝከኝ አስከ ለዘላለም
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ኅዋላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
የዘላለሜ ነህ ሁሉም ሲቀር ኅዋላ
መልህቅ የሆንከኝ ግራ እንዳልጋባ
መልህቄ (፬×)
ያዝከኝ እየሱሴ
መልህቄ (፬×)
ያዝከኝ እየሱሴ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя