ክንዳቹ አይላላ ጉልበታቹ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
የናዝሬቱ እየሱስ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
ክንዳቹ አይላላ ጉልበታቹ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
የናዝሬቱ እየሱስ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
ከግብፅ ከባርነት ከፈረኦን ግዛት
ህዝቡን ያሳረፈ ከጭንቀት ከፍርሃት
በእሳት በደመና በቀን ሌት እየመራ
ያው የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
መንገዱ እጅግ ሩቅ ቢመስል ሚከብድ ማያልቅ
የዓለም ኑሮ ፈተና ቢሆንም ትንቅንቅ
ከእኛ ጋር ያለው ዓለምን አሸንፏል
እስከ ፅሆን ድረስ በድል ይመራናል
ክንዳቹ አይላላ ጉልበታቹ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
አማኑኤል እርሱ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የወጡ ወደ ሰልፉ
የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእሳትን ኃይል አጠፉ
በቅንም ፈረዱ መንግስታትን ድል ነሱ
ዓለምን ኮነኑ ጣኦትን ፈረሱ
ዛሬም ከበዉናል እነርሱ እንደ ደመና
ክንዳችን እንዳይልላላ ጉልበታችን ይፅና
የፃድቅ ጉልበቱ ነዉና እምነቱ
ቅዱሳን ካህናቱ እልፍ በሉ በርቱ
ክንዳቹ አይላላ ጉልበታቹ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
ተስፋውን የሰጠው አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
ኃይልን በሚሰጠን ሁሉን እንችላለን
በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን
ኃይልን በሚሰጠን ሁሉን እንችላለን
በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን
ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና
አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነዉና
ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና
አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነዉና
ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና
አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነዉና
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
አማኑኤል እርሱ አለ ከእኛ ጋራ (፪×)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя