Kishore Kumar Hits

Tekeste Getnet - Sew Kentu текст песни

Исполнитель: Tekeste Getnet

альбом: Deg Neh , Vol. 5


ባጎረሰ እየተነከሰ
እቤት ዋለ ስንቱ እያለቀሰ
ለክፉ ቀን ነበረ ወዳጁ
ግን ተገኘ ሲሸምቅ ከደጁ
ከገበታው ላይ የበላ
ተረከዙን ደግሞ ቢያነሳ
ለትምህርት ተጽፏል በቃሉ
ገሮች ሆይ ይህንን ልብ በሉ
ሳኦል አስተካክሎ ስል ጦሩን
ወረወረ ሊገድል ዳዊትን
አምላክ አተረፈው ገብቶ ጣልቃ
የወንድምም ክፉ አለ ለካ
ይቅር አይወራ ክፉ አትናገር
ልመድልኝ ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር
ጉድጓድን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት
ጊዜ እስኪያስተምረው አንተ አትፍረድበት
ይሁን አይወራ ክፉ አትናገር
ልቤ አስተውል ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር
ጉድጓድን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት
ጊዜ አለው ለሁሉ ተው አትፍረድበት
ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ መሆኑ ገብቶኛል ሰው ከንቱ
ቢጠበብ ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ቢያስተውል ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ጌታ ካልረዳው ከንቱ ከንቱ
ልቡን ካልያዘው ከንቱ ከንቱ
መስዋዕቱን ጌታ ችላ ቢለው
ተቆጥቶ ወንድሙን ገደለው
ያድርግ እንጂ እሱ እንደፈቀደ
አንዱን ትቶ አንዱን ከወደደ
ወንድምህን ወዴት አረከው
እንዳላየ ሆኖ ቢጠይቀው
አይደለሁም የሱ ጠባቂ
ብሎ መለሰ ያ አላዋቂ
ደሙ ጮክ ብሎ አወራ
ያለበደል ምነው ግፍ ተሰራ
ተንከራታች ሆነ በምድር ላይ
እግዚአብሔር አይቷል ሰው ባያይ
ይቅር አይወራ ክፉ አትናገር
ልመድልኝ ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር
ጉድጓድን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት
ጊዜ እስኪያስተምረው አንተ አትፍረድበት
ይሁን አይወራ ክፉ አትናገር
ልቤ አስተውል ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር
ጉድጓድን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት
ጊዜ አለው ለሁሉ ተው አትፍረድበት
ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ
ሰው ከንቱ መሆኑ ገብቶኛል ሰው ከንቱ
ቢያገኝም ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ባያገኝ ከንቱ ከንቱ ከንቱ
ጌታ ካልረዳው ከንቱ ከንቱ
ልቡን ካልያዘው ከንቱ ከንቱ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители