Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Yegeta Wud Lij текст песни

Исполнитель: Meskerem Getu

альбом: Mengistih Timta


የመዳን ሚስጢር ትፈቶልህ
ኢየሱስ ነግቶ በትላንትህ
ከፍቅሩ ስንቴ ተጽናንተሃል
ሁሉን ትቶ ከጐንህ ቆሞልሃል
ዛሬ ምን ስንፍና ተበተበህ
አጥርተህ እንዳታይ ዓይንህን ከለለህ
ከዘላለሙ ይልቅ ለሚያልፈው ተገኘህ
ጌታን በመተውህ እንደምን ተሞኘህ
የጌታ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ
ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ
የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ
ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ

ብርሃንን ትተህ ወደ ጨለመበት ትገሰግሳለህ
የነፍስህን ሰላም ከማታገኝበት ሰፈር ትሮጣለህ
ምንስ ብትኮበልል ከኢየሱስ ፍቅር ወዴት ትሸሻለህ
ለአንተ ሲል አይደል ወይ ነፍሱን የሰጠልህ በመስቀል የወለ
የአባቴ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ
ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ
የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ
ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ

የመዳን ሚስጢር ትፈቶልህ
ኢየሱስ ነግቶ በትላንትህ
ከፍቅሩ ስንቴ ተጽናንተሃል
ሁሉን ትቶ ከጐንህ ቆሞልሃል
ዛሬ ምን ስንፍና ተበተበህ
አጥርተህ እንዳታይ ዓይንህን ከለለህ
ከዘላለሙ ይልቅ ለሚያልፈው ተገኘህ
ጌታን በመተውህ እንደምን ተሞኘህ
የጌታ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ
ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ
የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ
ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ

እንዴት ሊሆን ሰበብ የአንተ መገፋት ቢነሳብህ ዱላ
ይከፍል የለ ወይ ለሁሉ እንደስራው ብትታገስ ኋላ
ወንድሜ ተመለስ ጌታ ነው ሚበጅህ ምን ቢበዛ ሰልፉ
ዛሬም ይወድሃል ፍቅሩ አልቀነሰም ግባ ወደ እቅፉ
የአባቴ ውድ ልጅ የገዛህ በደሙ
ካሰረህ እስራት ያድንሃል ስሙ
የተበትበህን በጣጥሰህ ተራመድ
ከነፍስህ አብልጠህ ዓለም አትውደድ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители