መንግስተ ሰማይ መንግስተ ሰማይ
መንግስተ ሰማይ መንግስተ ሰማይ
እንደምን ናፍቀናል መዳኒታችንን
በአይናችን ልናይ ፊት ለፊት ልናይ
አሁንስ ጓጉተናል ከሞት ያዳንከንን
ባይናችን ልናይ ፊት ለፊት ልናይ
♪
በዚያ ሀዘን የለም መከራና ለቅሶ
መከፋት መጨነቅ ያበቃል ጨርሶ
አዎን እንሄዳለን ወደ እየሩሳሌም
በደስታ በሐሴት ልንኖር ዘላለም
መንግስተ ሰማይ መንግስተ ሰማይ
መንግስተ ሰማይ መንግስተ ሰማይ
እንደምን ናፍቀናል መዳኒታችንን
በአይናችን ልናይ ፊት ለፊት ልናይ
አሁንስ ጎጉተናል ከሞት ያዳንከንን
ባይናችን ልናይ ፊት ለፊት ልናይ
♪
ያልበቃን ስንሆን ብቁ ሆነን ታይተን
ሕይወት ያለበስከን ሞታችንን ሞተህ
ዳግመኛ ምትመጣ ታጅበሕ በመላዕክት
መቼ ይሆን ቀኑ አንተን ምናይበት
ጽኑነዉ ተስፋችን ስንጠብቅህ ልናይህ እንደገና
ትመጣልናለህ አለኝታችን በክብር በደመና
አሜን ማራናታ ቶሎ ናልን አትዘግይ የኛ ጌታ
ልጆችህ ናፍቀናል ልንዳስስህ እጆችህን ልንነካ
ኢየሱስ ሆይ ናልን ኢየሱስ ሆይ ናልን
ኢየሱስ ሆይ ናልን ሀገራችን ዉሰደን
ልናይህ ናፍቀናል ልናይህ ናፍቀናል
ልናይህ ናፍቀናል ልናይህ ጓጉተናል
ማራናታ አሜን መንግስትሕ ትምጣልን
ጽኑ ነዉ ተስፋችን ስንጠብቅህ ልናይህ እንደገና
ትመጣልናለህ አለኝታችን በክብር በደመና
አሜን ማራናታ ቶሎ ናልን አትዘግይ የኛ ጌታ
ልጆችህ ናፍቀናል ልንዳስስህ እጆችህን ልንነካ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя