Kishore Kumar Hits

Meskerem Getu - Wedante Erotalehu текст песни

Исполнитель: Meskerem Getu

альбом: Wedante Erotalehu


የአለም ምናምንቴ አይስበኝም ከቶ አያምረኝም
የሚያብረቀርቀው አይገዛኝም ከቶ አያታለኝም
በሚያልፈው በሚጠፋው አልማልልም ከቶ አልጎመጅም
ሃሳቤ ተወርሷል ባንተ በኢየሱስ ነፍሴን የሚያረካት ፍቅርህ ነው በፊትህ መፍዘዝ
እወድሃለሁ ከውስጤ ካንጀቴ ኣንተ ብቻ እኮ ነህ የሞላኸው ቤቴን
ብዬ ብዬ አልጠግብ ስላንተ ባወራ
የህይወት ውሃ ነህ የህይወት እንጀራ
እራብሃለሁ
እራብሃለሁ
ጌታ መድሃኒቴ አንተን እሻለሁ
እጠማሐለሁ
እጠማሐለሁ (ፈልግሃለሁ)
ኢየሱስ መድሃኒቴ አንተን እሻለሁ

የጸዳልህ ብርሃን ሚናፈቀው ክብርህ
የልቤን ተማጥኖ እንዳየው ያያል ፊትህን
መጠየቂያ ያለኝ ከእጅህ እንድቀበል
ግን እንዲያው ዝም ብዬ ከእግርህ ስር ቁጭ ልበል
ገና በማለዳ ወዳንተ እሮጣለሁ የመንፈስህ እሳት ህይወቴን ያግለው
ልማር እሻለሁ እንዳውቅህ አጥብቄ
ከህልውናህ ጋር ልቅር ተጣብቄ
ፈልግሃለሁ
ፈልግሃለሁ
እስካገኝህ ድረስ እጣደፋለሁ
እጠማሀለሁ
እጠማሀለሁ (ፈልግሃለሁ)
ፈልግሃለሁ ጌታ መድሃኒቴ አንተን እሻለሁ

ክብሬ ነህ አዶናይ ቀኔን ምታፈካ
የምትሰጠው ደስታ በምንም የማይተካ
አብሮነትህ እኮ ነው ህይወቴን ያጣመ
ዛሬም ልቤ አንተን አንተን ብቻ አለመ
ገና በማለዳ ወዳንተ እሮጣለሁ
የመንፈስህ እሳት ህይወቴን ያንድደው
ልማር እሻለሁ እንዳውቅህ አጥብቄ
ከህልውናህ ጋር ልቅር ተጣብቄ
እወድሃለሁ ከውስጤ ካንጀቴ
ኣንተ ብቻ እኮ ነህ የሞላኸው ቤቴ
ብዬ ብዬ አልጠግብ ስላንተ ባወራ
የህይወት ውሃ ነህ የህይወት እንጀራ
እራብሃለሁ
እራብሃለሁ
ጌታ መድሃኒቴ አንተን እሻለሁ
እጠማሀለሁ
እጠማሀለሁ (ፈልግሃለሁ)
ኢየሱስ መድሃኒቴ አንተን እሻለሁ
ፈልግሃለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители