Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew - Abet Fikreh текст песни

Исполнитель: Dawit Getachew

альбом: Amnihalehu


የሀጢያተኞች ወዳጅ ጓደኛ
የጠፋውን ምትፈልግ እረኛ
የደሃ አደጎች ሁሉ አባት
ምታኖራቸው ባማረ ቤት
የመበለቲት ዋና ተሟጋች
ጠበቃ ነህ ለተጎዳች
ለተጨነቁ ሁሉ ደራሽ
የታመሙትን ደግሞ ፈዋሽ
አቤት ፍቅርህ ስንቱን ታደገ
ከጠፋንበት እየፈለገ
ቀና አደረገን ከሸክማችን
ፀጋህ ባይረዳን ጠፍተን ነበርን
ተማርኬ በፍቅርህ
አመልክሃለው ወድቄ ፊትህ
በፈቃዴ ደስ እያለኝ
ጌታ ኢየሱስ እወድሃለሁ
ቀኑ ሲመሽ ሰው ሁሉ ሲሄድ
የማትቸኩል ለቁጣ ለፍርድ
የውስጥ የልብን ሁሉ ተረድተህ
እንባን ከዐይን ታብሳለህ
አሮጌውን ልብስ አውልቀህ ጥለህ
የፀጋ ካባን ለኛ ደርበህ
እዳችንንም በመስቀል ከፍለህ
ያጸደከን እንዲሁ በፀጋህ
አቤት ፍቅርህ ስንቱን ታደገ
ከጠፋንበት እየፈለገ
ቀና አደረገን ከሸክማችን
ፀጋህ ባይረዳን ጠፍተን ነበርን
ተማርኬ በፍቅርህ
አመልክሃለው ወድቄ ፊትህ
በፈቃዴ ደስ እያለኝ
ጌታ ኢየሱስ እወድሃለሁ
እኔም ዋና ምስክር ነኝ
አውቃለሁ ከየት እንዳነሳኸኝ
በፍቅር እጆችህ እጆቼን እየያዝክ
ከስንቱ ጥፋት መለስከኝ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители