Dawit Getachew - Beki Neh текст песни
Исполнитель:
Dawit Getachew
альбом: Amnihalehu
ምን ቀረኝ ከእንግዲህ ሁሉን ሰጠኸኝ
የመንግሥትህ ወራሽ በልጅህ ሆንኩኝ
ከአንተ የተነሳ ተስፋዬ ሙሉ ነው
በሚያስጨንቅ ዘመን ቆሜ ስቃለው
አንተን እንጂ ሁኔታን ከቶ አላይም
በእምነት እንጂ በሚታየው አልሄድም
እረፍትና ሰላም የመንፈስም ደስታ
ፍለጋ አትሄድም ነፍሴ ከአንተ ወጥታ
ዝማሬዬ ነህ የልቤ ደስታ
ነፍሴ ረክታለች ውዷን አግኝታ
ከበቂም በላይ በአንተ አርፌያለሁ
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
♪
በአንተ ሁልጊዜ ደስ ደስ ይለኛል
በአብሮነትህ ልቤ ይጓደዳል
እጅህ በሰራት በዚች ቀን ላይ ቆሜ
አመሰግናለሁ ስለ ሰላሜ
ሀብት ቢሞላ ቢትረፈረፍ ከንቱ ነው
ሰላምን ከምንጩ ጨልፎ አያመጣው
በሁሉ ሁልጊዜ ደስ የሚያሰኘኝ
የአንተ ሰላም ነው በክርስቶስ ያለኝ
ዝማሬዬ ነህ የልቤ ደስታ
ነፍሴ ረክታለች ውዷን አግኝታ
ከበቂም በላይ በአንተ አርፌያለሁ
እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው
♪
የማያቋርጥ እረፍት የማይነጥፍ ደስታ
በማዕበል ውስጥ እረፍት በመናወጥ ፈንታ
ከጸጋህ የተነሳ ዝም ብዬ እስቃለሁ
ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ተምሬያለሁ
የማያቋርጥ እረፍት የማይነጥፍ ደስታ
በማዕበል ውስጥ እረፍት በመናወጥ ፈንታ
ከጸጋህ የተነሳ ዝም ብዬ እስቃለሁ
ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ተምሬያለሁ
የማያቋርጥ እረፍት (የማይነጥፍ ደስታ)
በማዕበል ውስጥ እረፍት በመናወጥ ፈንታ
ከጸጋህ የተነሳ ዝም ብዬ እስቃለሁ
ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ተምሬያለሁ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя