Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew - Semhin Ebarikalew текст песни

Исполнитель: Dawit Getachew

альбом: Amnihalehu


ሁሉን የምትችል የዘላለም ንጉስ እግዚአብሔር
ያለህ የነበርህ ወደፊትም የምትኖር
ታላቅነት ሞገስ የሚገባህ ምስጋና ክብር
ኀይል ጥበብ ብርታት መንግሥት የአንተ ነው በሰማይ በምድር
ስምህን እንባርካለን ስምህን እንባርካለን
እግዚአብሔር አዳኝነትህን ዘውትር እንወድሳለን
በቅዱሱ ክንድህ አስመልጠኸናል
በድንቅ በተአምራት ማዳንህን አይተናል
ፀጋህ ባያግዘን ፍቅርህ ባይዘን
ምህረትህ ደግፎ እዚህ ባያደርሰን
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በቤትህ አኖረን
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በህይወት አኖረን
ሁሉ ከአንተ በአንተ ለአንተ ነው እኛ ምን አለን
የተቀበልነውን ከደጉ እጅህ እንሰጥሃለን
ስለቸርነትህ ስላረክልን ምን እንከፍላለን
እግዚአብሔር ሆይ ስምህን ለዘላለም እንባርካለን
ስምህን እንባርካለን ስምህን እንባርካለን
እግዚአብሔር አዳኝነትህን ዘውትር እንወድሳለን
ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን
በምህረት አምጥተህ ካህናት ያረከን
በኃያሉ ክንድህ አምልጠናልና
ዘውትር እንሰዋለን ለስምህ ምስጋና
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በቤትህ አቆመን
በጠፋን ነበረ አንተ ባትደርስልን
ግን ምህረት ቸርነትህ በህይወት አኖረን

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители