እኔ ግን አምላኬ ባንተ ደስ ይለኛል
ኃሴት ሆነኸኛል
ምህረትህን ታምኖ ልቤ አርፎብሃል
ሰላሜ ሆነሃል (ሰላሜ ሆነሃል)
ልቤ ጸንቶብሃል
ደስታዬ ሆነሃል (ደስታዬ ሆነሃል)
ውስጤ አርፎብሃል
በለስ እንኳን ባታፈራ
ቢጎድል የወይራ ስራ
እርሾችም መብልን ባይሰጡ
ምንም ባይገኝ በጋጡ
(እኔ ግን ኢየሱስ ባንተ ደስ ይለኛል አሃ)
(ኃሴት አደርጋለሁ ኃይል ሆነኸኛል)
አምላኬ ሆይ ወዳንተ መቅረብ ይሻለኛል
ያላንተ ዓለም ትርፉ ኃጥዕ ምኑ ያስቀናል
ወደ መቅደስህ ገብቼ ክብርህ አግኝቶኛል
በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ደስታህ ይበቃኛል
ወደ መቅደስህ ገብቼ ክብርህ አግኝቶኛል
በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ደስታህ ይበቃኛል
በለስ እንኳ ባታፈራ
ቢጎድል የወይራ ስራ
እርሾችም መብልን ባይሰጡ
ምንም ባይገኝ በጋጡ
(እኔ ግን ኢየሱስ ባንተ ደስ ይለኛል አሃ)
(ኃሴት አደርጋለሁ ኃይል ሆነኸኛል) እኔ ግን
(እኔ ግን ኢየሱስ ባንተ ደስ ይለኛል አሃ)
(ኃሴት አደርጋለሁ ኃይል ሆነኸኛል)
አንተ የሌለህበት ጥጋብ ተድላና ፍስሃ
ተጠምቶ እንደ መቃጠል ነው በደረቅ በርሃ
ልዩነቴ እኮ ነህ ጌታ ዓለመኞች ያጡህ
የምታረካ የሕይወት ዉሃ ነህ ለጠጡህ
ልዩነቴ እኮ ነህ ጌታ ዓለመኞች ያጡህ
የምታረካ የሕይወት ዉሃ ነህ ለጠጡህ
እኔ ግን አምላኬ ባንተ ደስ ይለኛል
ኃሴት ሆነኸኛል
ምህረትህን ታምኖ ልቤ አርፎብሃል
ሰላሜ ሆነሃል (ሰላሜ ሆነሃል)
ልቤ ጸንቶብሃል (ልቤ ጸንቶብሃል)
ደስታዬ ሆነሃል (ደስታዬ ሆነሃል)
ውስጤ አርፎብሃል (ውስጤ አርፎብሃል)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя