ፍልጌህ ፊትህን ብዬ
ፍልጌህ አንተኑ ብዬ
አልተመልስኩም ባዶ እጄን
ግን አረካኸው ውስጤን የልብ ጥማቴን
ሞልቶ እስከሚፈስ ባረከው ጓዳዬን ቤቴን
ባረከው ጓዳዬን ቤቴን
ሞላኸው ጓዳዬን ቤቴን
በእውነት አየሁኝ ካንተ በላይ ፍቅር እንደሌለ
በርግጥም አየሁኝ ካንተ ውጪ ህይወት እንደሌለ
ፍቅር አንተ ብቻ ነህ
ህይወት አንተ ብቻ ነህ
አላየሁም አልሰማሁም
ከልቡ ፈልጎ ያጣህም የለም
እኔ ምስክር ነኝ ጌታዬ ፈልጌ አግንቼህ
በህልውናህ አጥለቅልቀህ ህይወቴን ለወጥህ
እኔ ምስክር ነኝ ከልቤ ፈልጌ አግንቼህ
በህልውናህ አጥለቅልቀህ ህይወቴን ለወጥህ
በእውነት አየሁኝ ካንተ በላይ ፍቅር እንደሌለ
በርግጥም አየሁኝ ካንተ ውጪ ህይወት እንደሌለ
ፍቅር አንተ ብቻ ነህ
ህይወት አንተ ብቻ ነህ
በእውነት አየሁኝ ካንተ በላይ ፍቅር እንደሌለ
በርግጥም አየሁኝ ካንተ ውጪ ህይወት እንደሌለ
ፍቅር አንተ ብቻ ነህ
ህይወት አንተ ብቻ ነህ
በድፍረት በነፃነት
እገባለው ካለህበት
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя