ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ ስታንኳኳ ፡ በሬን
ግን ፡ አላስተዋልኩም ፡ አንተ ፡ መሆንህን
ብዙ ፡ አድክሜሃለሁ ፡ አውቃልሁ ፡ እራሴ
ግን ፡ እራርተህልኝ ፡ ቤቴ ፡ ትመጣ ፡ ይሆን
አዝ:- እጠብቅሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ
በመጠበቂያዬ ፡ ላይ ፡ ዳግም ፡ እስክትመጣ
ድምፅህን ፡ አሰማኝ ፡ ልቤ ፡ እንዲፅናና
ግን ፡ አንተ ፡ ዝም ፡ ካልከኝ ፡ እፈራለሁና
♪
ዝም ፡ ስትል ፡ ጊዜ ፡ ስታጠፋ ፡ ድምጽህን
ያሰብኩት ፡ በሙሉ ፡ እንዳልነበር ፡ ሲሆን
ቀኑ ፡ ሲጨላልም ፡ ፈርቼ ፡ ይህን ፡ ሁኔታ
መልዕክት ፡ ልኬ ፡ ነበር ፡ ትመጣ ፡ ይሆን ፡ የሚል
አዝ:- እጠብቅሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ
በመጠበቂያዬ ፡ ላይ ፡ ዳግም ፡ እስክትመጣ
ድምፅህን ፡ አሰማኝ ፡ ልቤ ፡ እንዲፅናና
ግን ፡ አንተ ፡ ዝም ፡ ካልከኝ ፡ እጠፋለሁና
♪
እንግዳዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እረፍ ፡ ቤቴ ፡ ገብተህ
ብዙ ፡ የምነግርህ ፡ አለኝ ፡ ማጫውትህ
ልቤ ፡ አንተ ፡ ቤት ፡ ነው ፡ ሀሳብህን ፡ ፈፅም
እጠብቅሃለሁ ፡ ከቶ ፡ አልሰለችም
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя