Kishore Kumar Hits

Dawit Getachew Abreham - Diro Gena текст песни

Исполнитель: Dawit Getachew Abreham

альбом: Etebikihalew


ድሮ ፡ ገና ፡ ከማህፀን ፡ ሳለሁ ፡ በእናቴ ፡ ሆድ
በሥም ፡ ጠርተህ ፡ የለየኸኝ ፡ ክፉን ፡ ደጉን ፡ ሳላውቅ
የአንተ ፡ ክብር ፡ መገለጫ ፡ እንድሆን ፡ በቤትህ
ከነኃጢአቴ ፡ የመረጥከኝ ፡ ለአንተ ፡ እንድኖርልህ
በሰጠኸኝ ፡ መንገድ ፡ ስሄድ ፡ ባሰብክልኝ ፡ ስፍራ
እንዳልገኝ ፡ ሳሳዝንህ ፡ ቸል ፡ ብዬ ፡ ሳልሰማህ
ዛሬ ፡ በቀን ፡ ለምንሃለሁ ፡ ኃይልህ ፡ እንዲረዳኝ
በመክሊቴ ፡ ብዙ ፡ አትርፌ ፡ አንተን ፡ ደስ ፡ እንዳሰኝ
አዝ:- ኃይልህ ፡ ይርዳኝ ፡ ለምናለው
እንድትረዳኝም ፡ አምናለሁ
መልካም ፡ ነገር ፡ ያደረኩኝ ፡ መስሎኝ
ሳሳዝንህ ፡ እንዳልገኝ
ስመላለስ ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡ ሳገለግል ፡ አንተን
የማልኖረውን ፡ አውርቼ ፡ የተጣልኩ ፡ እንዳልሆን
እንዳታልፈኝ ፡ እፈራለሁ ፡ በምትመጣበት ፡ ቀን
ሕይወቴም ፡ አንተን ፡ ያክብርህ ፡ አፌ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን
ክብርህን ፡ አሳየኝ ፡ የአንተን ፡ ማንነት
ቅዱሱን ፡ መንፈስህን ፡ ሚመራኝ ፡ ወደ ፡ እውነት
እኔ ፡ ደካማና ፡ ኃጢአተኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ
ሃይልህ ፡ ግን ፡ ከረዳኝ ፡ ከእግሬ ፡ እቆማለሁ
አዝ:- ኃይልህ ፡ ይርዳኝ ፡ ለምናለው
እንድትረዳኝም ፡ አምናለሁ
መልካም ፡ ነገር ፡ ያደረኩኝ ፡ መስሎኝ
ሳሳዝንህ ፡ እንዳልገኝ
ቀድመህ ፡ ውጣ ፡ በሕይወቴ
ልከተልህ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ
አንተ ፡ ቀድመኀኝ ፡ ካልወጣህ
እኔ ፡ ብሮጥ ፡ ምን ፡ ላመጣ
ለምንሃለሁ ፡ ጌታ
ለምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ
ኃይልህ ፡ ይርዳኝ ፡ ጌታ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители