ዝም ያለ ዜማ መልእክት የሌለው
ለብ ጭጭ ያለ ጣዕም ወይም ምሬት የሌለው
ላርገቡት የሚነድ ለለኮሱት የጋየ
ድቅል ድብልቅ ፍቅር ለምን እንደሚኖር ያላየ
ልክ የማይጠይቅ እዉነትን አርቆ የጣለ
ከተከተተበት የማይዝል ግርዶሽ አድማሱ የሆነ
መንጋው ሁሉ ተለያይቶ ወደ ገደል ስጠብቅ ተራ
የሃይማኖት ካራ ጨብጦ እግዜር የኔ የኔ የኔ ይባላል
እግዚአብሔር አባል አደለም
እግዚአብሔር ድርጅት የለውም
የኔ ነው ባለ መቼ ሆነ
መፅሐፉ ይህን አላስተማረ
መዳኔ አዳኝ ስጦታ ነው
ቃል የገባው ለሁሉ ነው
በልጁ በኩል ላገኘው
አዳኝ አምላክ አባት ሚሆነው
በእርሱ ስራ ምክንያት እንግድነት የተሻረልን
መፃንነታችን ቀርቶ ባላገሮች የሆንን
እርቀን የነበርን ከቅርቦቹ ተዋህደን
አንድ ሆነን ከተፈጠርን
ለስልጣን ጥም ብሎ ህዝብን ከህዝብ መለያየት
ትምርተ ልዩ እያሉ ራስን አግንኖ ማየት
ለሰነፍ ጧሪ ክምችት ቤተስቡ ቢጓተት ቢጣላ
የሚከፍል ይጠየቃል ኃዋላ
የጥንቱ ነኝ
አንባቢም ነኝ
ዓለም አቀፍ ነኝ
አይሰራም
የፀጋ ነኝ
የትጋት ነኝ
የእምነት ነኝ
አይሰር አይሰር አይሰራም
እግዚአብሔር አባል አደለም
እግዚአብሔር ድርጅት የለውም
የኔ ነው ባለ መቼ ሆነ
መፅሐፉ ይህን አላስተማረ
ስጦታ ነው
ቃል የገባው ለሁሉ ነው
በልጁ በኩል ላገኘው
አዳኝ አምላክ አባት ሚሆነው
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя