Kishore Kumar Hits

Jemberu Demeke - Esat Ena Wuha текст песни

Исполнитель: Jemberu Demeke

альбом: Jemberu Demeke


ተው ማነህ ተው ማነህ
ተው ማነህ ተው ማነህ
የተኛውን ለቤን ትቀሰቅሳለህ
ከእንግዲህ ብቻዬን ብለህ እንዳላልከኝ
ደንገት መተህ ደግሞ ምን አርጊ ምትለኝ?
እንደ እግር አይደለም ይህ ልብ
ታሸቶ እንኳን አይሽርም
ቀድሞ ነበር እንጂ ከርሞውን ማቀድ መወጠን
ክረምት ኬደ ወዲ ቢገናኝ በሬና ሞፈር
ከየት አምጥቶ ሊያበቅል ሊያፈራ ያገሬ ምድር
አንችዬ ጡር አይደለም ዎይ ፍቅርን መግፋትና
አጥፍቶ ይቅርታን ላለ ፊት ማዞር መጨከንማ
ቢያመጡም ፍቅር ከናፍቆት ዳግመኛ ተገጣጥመው
ቢያውቁ ነው የልቤን እሳት የሚያቀፅፍ ፍቅር ውሃ እንዳለው
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ

ምጣኔ ነች ህይወት ትርጉም የምትሰጠው
እሷ ባትኖር እኮ ግጥሜንም እንኳን አልፅፈው
ምጣኔ ነች ህይወት እሳትና ውሃ
አስቡት መኖርን በበረዶና በረሃ
ምጣኔ ነች ህይወት እውነትና ሃሰት
ሃሰት ግን ከሌለ ለኛ ምን ሊበጀን እውነት
ምጣኔ ህይወት ነው ምለው ለምንድነው?
ሁሉን አመጣጥኖ ፈጣሪ ስለፈጠረው ነው
እናም ሰው
እድሜ ዘመኑን ይኖራል ምጣኔን ሲፈልገው
እናም ሰው ሳያውቀው
በመቃጠል ይኖራል ውሃን እያናናቀው
እናም ሰው ተቃጥሎ
ጭራሽ ብሎ ይገባል ወደ ባሰው በረዶ
ይህም ሰው ሲበርደው
ተመልሶ ይመጣል ያን ፍቅሩን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ
አሳዶ ፍቅርን አሳዶ
አሳዶ መውደድን አሳዶ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители

Tsedi

Исполнитель

Ahadu

Исполнитель