Kishore Kumar Hits

Jemberu Demeke - Ye Etege Chewata текст песни

Исполнитель: Jemberu Demeke

альбом: Jemberu Demeke


ሰጥታ አትሰጠኝ በምኞት ውሰጥ ታኖረኛለች
ስጠራጠራት እንድተዋት ትፈቅድልኛለች
እንዴት እንዲ ይሆናል? ብዬ ሳስበው
እሷን መተው ሞትን መምረጥ እንደሆነም ታውቃለች
በታዳጊነት ኑሮን ማን ያውቃታል ዘንድሮ
ሊያናግራትም ይፈራል ስንቱ በቃሉ ፎክሮ
ስንቱ በቃሉ ፎክሮ ሲያያት ግን ይደነግጣል
ውበት ብቻ ተከትሎ ውሰጧን ሳያየው ይቀራል
"እንዲህ በመሆኑ እሷ ታድያ ምን ታደርጋለች?"
ፈሪውን አስጨንቃ ደፋሩን ግን ትከሳለች
"እንዲህ በመሆኑ እሷ ታድያ ምን ታደርጋለች?"
ጭሰት ያምርብሀል ብላም በጭስ ትደብቃለች
"እንዲህ በመሆኑ እሷ ታድያ ምን ታደርጋለች?"
አርቆ ማሰብን ከአዕምሮአችን ታርቃለች
"እንዲህ በመሆኑ እሷ ታድያ ምን ታደርጋለች?"
አይኖቻችንን ዘግታ አለምን ታሳየናለች

እኔም
አይኖቼን ስገልጥ
ውስጣዊ ውበቷ መታየት ጀመረ ይበልጥ
ትርጉሙ የማንነቷ ወደ አእምሮዬ ስር ሲሰድ
ያ ውስጣዊ ውበቷ መታየት ጀመረ ይበልጥ
እኔም
አይኖቼን ስገልጥ
ውስጣዊ ውበቷ መታየት ጀመረ ይበልጥ
ትርጉሙ የማንነቷ ወደ አእምሮዬ ስር ሲሰድ
ያ ውስጣዊ ውበቷ መታየት ጀመረ ይበልጥ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители

Tsedi

Исполнитель

Ahadu

Исполнитель