ማን ውስጤን ያውቃል?
ማን ውስጤን ያውቃል የሚያየው ፊትለፊቱን
ሰው ግን እኔን ያማል
ጀምበሩን የሚጣላ አይነጋለትም ለሊቱ
ነገር ምን ያደርጋል?
ብል
ላይገባቸው ነገር ነው ማወራው ለነገሩ
እንኳን ሚረዳ ሊመጣ
የለም መጥቶም የሚረዳ
ማስመሰል ለመወደድ
መያያዝ ለመቀደድ
ከራሳችን ማንነት
ለሰው ብሎ መሰደድ
ታድያ በማን ይፈረድ
የውስጡን ሲያወራ ብለውት ተረት ተረት
እውነተኛው ተራ እየነፉበት ደረት
እኔስ አለኝ መላ አንደበቴ ይከፈት
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
ኩነኔን ብናይ
መች ያልቃል
ነፍሳችን ወደላይ መች ይለምናል?
ድብቅ አደርባይ ሆነናል
እንዲሁ በዝምታ በሩን ዘግተን ቆመናል
በባዶ
ሁሉም ሰው መበደሉን ተዋህዶትም ቆመናል
በዝምታ
ዝምታ ወርቅ ነው ብለን ልባችን ሳይረታ ግን ቆመናል
ግን አትፍራ
ግን አትፍራ
ግን አትፍራ
አትፍራ ተናገር!
ማንስ ቀናው አንገቱን ደፍቶ
አትፍራ ተናገር!
ምን ተሰማው ዝምታን መርጦ
አትፍራ ተናገር!
ባናወራ እንኳን እንቶ ፈንቶ
አትፍራ ተናገር!
ቅጥፈት ባዩ አይጠፋም ከቶ
አትፍራ ተናገር!
ቅጥፈት ቢሉት እሴቱ አይጠፋ
አትፍራ ተናገር!
ቀና ብትል መጥቶ አይደፋህ
አትፍራ ተናገር!
እኔም አንደበቴን ከፍቼ
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
አንዴ ልናገር የውስጤን
አንዴ ልናገር የልቤን
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя