አቤት አቤት አቤት
አቤት የሷስ ውበት
ከተማው ያራዶች ቤት
ጉድ ሆነ በሷ ውበት
ጩኸት ያስተጋባል የገደል ማሚቱ
እሷን ብዬ ጮኩኝ የታለች ልጅቱ
ንጠው ንጠው ለዩት አይቡን ከ አሬራ
መክንከኔን አውቆ ጠፋ የሚያወራ
ድኙን አጨሱልኝ በሽታ መስልዋቸው
እሷ እንዳመመችኝ ማን በነገራቸው
እንዴት ያደርጉታል የ ሆድን ህመም
ማጭድ አይገባበት በጅ ኣይታረም
ጫካውን አልፈራ ከ ደኑ ዘልቄ
አውሬ ቢያጏራብኝ ድንቅ አይደለ ብርቄ
ሰውን ጉድ አስባለው አንቺ ስር መውደቄ
ቅረቢ ከ ጎኔ እንደ ግርማ ሞገስ
እንጀራም ያላይን መች ይላል እና ደስ
ያንቺስ ውዴ ክፉኛ ከባድ ነው
አንቺን ብቻ ሌተ ቀን የምለው
አቤት አቤት ባንቺ ስንቱን አየው
አቤት አቤት ብዙ ተሰቃየው
አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት መውደድ አቤት አቤት
አቤት አቤት ፍቅር አቤት አቤት
የ ስሜቴ ጌታ የ ልቤ ባለቤት
የምወዳትን ልጅ አርግልኝ ጎረቤት
ሰበዝም ሰምበሌጥ ፊደል ነው የለያቸው
መውደድም ፎንቃ ነው ስም ቅፅል ያው ናቸው
ጠዋት ያዩት ጤዛ ማታ ቢሰለብም
ልብ የገባን ፍቅር ማውጣት አይታሰብም
ኬሻውን አንጥፌ እደጇ ልተኛ
ቅዠቱ ባይተወኝ ጋብ ይበልልኛ
ካቻማሌው መጣ ተጉዞ ተጉዞ
አይኗ ሆነኝ ጠላት አፍዞ አደንግዞ
ጥርሷም አሰከረኝ ወዝውዞ ወዝውዞ
የት አሉ ሹማምንት የት አሉ ጌቶቹ
ካንጀት ኣማካሪ ጠፉ ጠቢቦቹ
ዝናር ከወገቡ የማይጠፋው ጀግና
ትጥቁን አስፈታሺው ሆነሽው ፈተና
ያንቺስ ውዴ ክፉኛ ከባድ ነው
አንቺን ብቻ ሌተ ቀን የምለው
አቤት አቤት ባንቺ ስንቱን አየው
አቤት አቤት ብዙ ተሰቃየው
አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት መውደድ አቤት አቤት
አቤት አቤት ፍቅር አቤት አቤት
የ ስሜቴ ጌታ የ ልቤ ባለቤት
የምወዳትን ልጅ አርግልኝ ጎረቤት
አይን አይከሰስ ደሞ በማየት
እዳው ለልብ ነው እንደ ሞት ሽረት
ከውቢትዋ ዘሮች የሴት እመቤት
ስሜም ባንቺ ይጥፋ
ስጠራሽ አቤት
ስጠራሽ አቤት
ስጠራሽ አቤት
ስጠራሽ አቤት
ስጠራሽ አቤት
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя