ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ
እንዴት ነሽ ልበልሽ
እንዴት ነሽ በሞቴ
ላጫውትሽ በስሱ
እስኪ ሳይዝልም ጉልበቴ
ዜማ አዲስ አባዊ
ጨዋታው የአራዳ
ቆንጆ አይቶ ያለፈ ቀረበት ተጐዳ
ሀገሩ ሁሉ ቆንጆ ሸጋ ሸጋ ብቻ
ጠይቅ ተጠየቅም እንጂ ተከተትም ካሻህ
ከሰፈር ከተማ አይዞህ ውሎ ካማረለት
ወንድ ልጅ ወንድ ነው ለሴቷ ነው ውበት
ወይ እቺ ማርዬ ወይ እቺ አረንቻታ
አብረከረከችኝ እኔን በጉልበቴ ገብታ
ኧረ እንዴት ነው ቀኑ ኧረ እንዴት ነው ማታ
ዘዴማ አላጣም እኔ ለያዝሽው ጨዋታ
በለበሽው ቀሚስ ባደረግሽው ጫማ
ዐይን ሁሉ ማረፊያ አንቺ ላይ ሆነና
አኔን ረረሳሽኝ ኸ ወዳጅሽ በዛና
አውቃለሁ ልንገርሽ ቆንጂት የኔው ነሽ በኋላ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ
እስኪ ሂጂ ደሞ ሰላምታዬ ግቢ
ቃሊቲ መስመር ላይ ካለው ትልቅ ግቢ
ያልነካካ የለም መጥቶ ተመካሪ
ያላጠፋ የለም አጥፍቶ ታራሚ
እኔም ነበርኩበት ከሌላኛው ግቢ
አሁንም ልድገመው ይግባ ሰላምታዬ
ማረሚያ ላላችሁ እህትም ወንድሞቼ
ያሳጥረው ቀኑን መውጫውንም ብዬ
መቼ ቀርቶ ያቃል እኔማ ፀሎቴ
ቢመቱም መዶሻ ቢፈርዱም ዳኝዬ
መውጫው አይታወቅም አይዞኝ የሰው ልጅ ወዳጄ
ለጊዜው ነው እንጂ እራስ እስኪገዛ
መኖርያም አይደልም ያላችሁበት ቦታ
ወገን ጠንከር ነው በሉ በርታ በርታ
ከአለም በቃኝ ግቢ ድጌማ ላይገባ
ቢሳሳት አንዴ ነው በሉኝ ነቄ እና አራዳ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ
እርም እርም ይላል ሲሄድ በፈረስ
የድሮው አራዳ ወይ ኃብተ-ጊዮርጊስ
እርም እርም ይላል ሲሄድም በዶጅ
የድሮው አራዳ የፒያሳው ልጅ
እርም እርም ይላል ይታያል ከሩቅ
የድሮው አራዳ ከዐይንም አይርቅ
እርም እርም ይላል ይግላል መንገዱ
ስቆ አዳሪ ሁሌም የአራዳ ልጅ ደጉ
እርም እርም ይላል ይጨሳል ሰፈሩ
የ ጃንሜዳ አራዳ መጥቶ ሄደ ቢሉ
እርም እርም ይላል የዛ ሰው ጨዋታ
የደጃች ውቤ ልጅ የዛ የሰው ደስታ
እርም እርም ይላል እርምጃ እና ልቡ
የካዛንቺስም ልጅ ፍቅር ነው ቀለቡ
እርም እርም ይላል ሱሪ እና ጃኬቱ
ወረድ በል እስኪ ደግሞ ወይ እሪ በከንቱ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
እንደስሙ አዳሪ እንዳንቺ አለ ወይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ ኤይ
አዲስ አበባ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя