ከአራት ኪሎ ቤላ
♪
ተጫወቺ በይ ተጫወቺ ተጫወቺ በይ
ሁሉም ያንቺዉ ነዉ ያዢ በርቺ ተጫወቺ በይ
ጠጋም ገባም በይ ጠጋም ገባ ጠጋም ገባም በይ
ሳቅም ጨዋታሽ ላገር ይታይ ጠጋም ገባም በይ
ምርቃቴ ነሽ ስጓዘዉ በወኔ
ሲጠሯት ሰማዉኝ እሷንም እንደ እኔ
እኔስ ደና ነበርኩ እሷም ደና ልጅ
አመሏ ከአመሌ ባይገጥም ነዉ እንጂ
ያገር የከተማዉ የሰፈሩ ራፐር
ብላ ትጣራለች ፍቅሯ ሲጨማምር
ደሞ መለስ አርጋ ስትለዉጥ ባህሪ
ብላ ትጣራለች አንተ ክፉ አዝማሪ
አንዳንዴ ተጫዋች አንዳንዴ አኩራፊ ነሽ
እኔ እወድሻለሁ በሁለቱም አመለሽ
ተጫወቺ በይ ተጫወቺ ተጫወቺ በይ
ሁሉም ያንቺዉ ነዉ ያዢ በርቺ ተጫወቺ በይ
ጠጋም ገባም በይ ጠጋም ገባ ጠናም ገባም በይ
ሳቃም ጨዋታሽ ላገር ይታይ ጠጋም ገባም በይ
♪
መዉደዴን እንቺ ብዬ ብሰጣት ደነቃት
አየች አየችኝ እና ገረማት አስደነቃት
መቼም አይመጣዉም ነዉ መዉደዱ ከሱ አይነት
እስኪ እኔ ልስጥሽና ቅመሺና መልሻት
♪
ከአራት ኪሎ ቤላ ስትመላለሺ
ጃን ሜዳን አታዉቅም በሎ ሰዉ አማሽ
የቤት ልጅ ጨዋታ ወግ ወጉን ይዘሽ
ማን ያዉቃል ያለኔ እሳት እንደሆንሽ
አይደለም እንዴ በአለምዬዉ ዜማ
ዋሽዉ እንዴ አይደለም እንዴ
ዋሸዉ እንዴ አይደለም እንዴ
አንቺን ነው አንቺን ነዉ አንቺን ነዉ ያየሁሽ
ቀልቤን ወስደሽ ማርከሽኝ
አንቺ አንቺን ያሰኘሽኝ
አንቺን ነው አንቺን ነዉ አንቺን ነዉ ያየሁሽ
ቀልቤን ወስደሽ ማርከሽኝ
አንቺ አንቺን ያሰኘሽኝ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя