ሃጥያት ፡ አላገኘህም
ስንፍና ፡ አልከሰሰህም
ስትገዛ ፡ አልደከመህም
እርጅና ፡ አላወቀህም(፪)
እኔም ፡ አላውቅህም ፡ የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አይመረመርም(፪)
እኔም ፡ አላውቅህም ፡ የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አይመረመርም(፪)
የለህም ፡ እኩያ
የለህም ፡ አምሳያ
ትልቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ(፪)
ትልቅ ፡ ነህ ፡ ሃሌሉያ(፬)
የነገሥታት ፡ ወገብ ፡ ትጥቅ ፡ የምታስፈታ
ሓያል ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ(፫)
የፍጥረት ፡ መገኛ ፡ ሕያው ፡ መሠረት
አትሰላ ፡ በዓመታት ፡ አትደመር ፡ በዘመናት
አትሰላ ፡ በዓመታት
የትኛውም ፡ ምሑር ፡ ሒሳብ ፡ አይሰራህም
የትኛውም ፡ ሰዓሊ ፡ ብሩሽ ፡ አይቀባህም
የቱም ፡ አንጠረኛ ፡ ቀርጾ ፡ አያወጣህም
አሐዱ ፡ አትባልም ፡ ደረጃም ፡ የለህም
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ለክብርህ ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ለዝናህ
ሽርጉድ ፡ ልበል ፡ ላገልግልህ
ጆሮዬን ፡ ልብሳ ፡ ልኑልርህ(፪)
ልኑርልህ(፬)
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ሞትን ፡ አሸነፈ
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ጨለማ ፡ ገፈፈ
እስቲ ፡ የማን ፡ ጀግና ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነሳ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ዙፋንህ ፡ የጸና
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጀግና ፡ ዙፋኑ ፡ የጸና
ዙፋንህ ፡ የጸና (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя