አዝ፦ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ
አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ
ከፍ ፡ የሚያደርግ ፡ አንስቶ ፡ ከውርደት ፡ ቦታ
አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግድለታለሁ
ተሸክሞኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ
ለዚህ ፡ ንጉሥ ፡ እቀኝለታለሁ
በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ
ምስኪን ፡ ችግረኛን ፡ እንደማንም ፡ ሳይተው
እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ስፍራን ፡ የሚሰጠው
የወደቀን ፡ ማንሳት ፡ ክብር ፡ የሆነለት
መታሰቢያም ፡ ሚያቆም ፡ ሰርቶ ፡ ታምራት
ባርኮ ፡ እየባረከ ፡ በእርሱ ፡ ደግነት
አክብሮ ፡ የሚያኖር ፡ ነው ፡ መልካም ፡ አባት (፪x)
አዝ፦ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ
አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ
ከፍ ፡ የሚያደርግ ፡ አንስቶ ፡ ከውርደት ፡ ቦታ
አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግድለታለሁ
ተሸክሞኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ
ለዚህ ፡ ንጉስ ፡ እቀኝለታለሁ
በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ
ምሕረቱን ፡ አብዝቶ ፡ ሞገስ ፡ የሚሰጥ
የጠላትን ፡ ከፍታ ፡ ወስዶ ፡ ሚያስረግጥ
በክንፎቹ ፡ ጥላ ፡ ሸሽጎ ፡ የሚያኖር
ተማምኖ ፡ ለተራው ፡ ስሙን ፡ የሚያከብር
እጅግ ፡ የሚራራ ፡ የበዛ ፡ እርዳታው
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ደግ ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ
አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ
ከፍ ፡ የሚያደርግ ፡ አንስቶ ፡ ከውርደት ፡ ቦታ
አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ
ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግድለታለሁ
ተሸክሞኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ
ለዚህ ፡ ንጉስ ፡ እቀኝለታለሁ
በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል
እንደሱ ፡ ጌታ ፡ እስቲ ፡ የታል (፪x)
እንደሱ ፡ ፍቅር ፡ እስቲ ፡ የታል (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя