Kishore Kumar Hits

Addisalem Assefa - Ere Enes Beyesus текст песни

Исполнитель: Addisalem Assefa

альбом: Yamelete Ene Negne


ህጉን ፡ ልተግብረው ፡ እንጂ ፡ በሕይወቴ ፡ ቃሉን ፡ ልኑረው
ያለኝ ፡ ሁሉ ፡ ይፈጸማል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለው
እራስ ፡ እንጂ ፡ ጅራት ፡ ላልሆን ፡ ቃሉ ፡ እንደሚለው
በስሙ ፡ የተጠራሁ ፡ ሰው ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ የኪዳኑ ፡ ሰው
አዝ፦ ኧረ ፡ እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንጂ
ያየሁት ፡ ውርደት ፡ አይደለም
ገና ፡ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ አያለሁ
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
እቸኩላለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
ወደ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ገና
በዐይኔ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
የጌታን ፡ ተአምር ፡ ገናና
እገሰግሳለሁ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ ፈጥኖ ፡ አንስቶኛል ፡ ከውድቀት
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ እርፉን ፡ ይዣለሁ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ክንዱን ፡ ተማምኖ ፡ እኔን ፡ ሲጠራ ፡ አሃሃ ፡ እኔን ፡ ሲጠራ
ያልተጸጸተ ፡ በእኔ ፡ ሊሰራ ፡ አሃሃ ፡ በእኔ ፡ ሊሰራ
መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ አቅንቶልኛል ፡ አሃሃ ፡ አቅንቶልኛል
ለብዙ ፡ ክብር ፡ ይፈልገኛል ፡ አሃሃ ፡ ይፈልገኛል
ቃሉን ፡ ሊያጸና ፡ ሊደግፈኝ ፡ አሃሃ ፡ ሊደግፈኝ
ከፊቴ ፡ ወጥቶ ፡ አይዞሽ ፡ ካለኝ ፡ አሃሃ ፡ አይዞሽ ፡ ካለኝ
ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ልፍራ ፡ ልኡሉን ፡ ይዤ ፡ አሃሃ ፡ ልኡሉን ፡ ይዤ
ልጓደድ ፡ እንጂ ፡ ስሙን ፡ መዝዤ ፡ አሃሃ ፡ ስሙን ፡ መዝዤ
እገሰግሳለሁ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ መቆም ፡ አልሻም ፡ መዘግየት
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ እርፉን ፡ ይዣለሁ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
አዝ፦ ኧረ ፡ እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንጂ
ያየሁት ፡ ውርደት ፡ አይደለም
ገና ፡ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ አያለሁ
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
እቸኩላለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
ወደ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ገና
በዐይኔ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና
የጌታን ፡ ተአምር ፡ ገናና
የሚዘጋና ፡ የሚከፍተው ፡ አሃሃ ፡ የሚከፍተው
መወርወሪያውን ፡ የሰበረው ፡ አሃሃ ፡ የሰበረው
ጠላቴን ፡ ሁሉ ፡ ተጣልቶልኛል ፡ አሃሃ ፡ ተጣልቶልኛል
ተከናወኚ ፡ ሂጂ ፡ ብሎኛል ፡ አሃሃ ፡ ሂጂ ፡ ብሎኛል
እንደመጣው ፡ ቃል ፡ አሜን ፡ ብያለሁ ፡ አሃሃ ፡ አሜን ፡ ብያለሁ
ባሕር ፡ ተከፍሎ ፡ እሻገራለሁ ፡ አሃሃ ፡ እሻገራለሁ
ሁሉን ፡ በሚያስችል ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ ፡ አሃሃ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ
እንዴት ፡ ብትሉ ፡ ኃይሌ ፡ የጌታ ፡ ነው ፡ አሃሃ ፡ ኃይሌ ፡ የጌታ ፡ ነ
እገሰግሳለሁ ፡ ወደ ፡ ፊትህ ፡ መቆም ፡ አልሻም ፡ መዘግየት
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ እርፉን ፡ ይዣለሁ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ላላይ ፡ ሌላ
አዝ፦ ኧረ ፡ እኔስ ፡ በኢየሱስ ፡ ክብር ፡ እንጂ
ያየሁት ፡ ውርደት ፡ አይደለም
ገና ፡ እርሱ ፡ ያየልኝን ፡ አያለሁ
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም
በሕይወቴ ፡ ጭንገፋ ፡ የለም

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители