ማዕበሉ ፡ ለምን ፡ ገፋኝ ፡ አልልም ፡ ይግፋኝ
ወጀቡ ፡ ለምን ፡ ነካኝ ፡ አልልም ፡ ይንካኝ
አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ
ሁሉን ፡ ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ
የነፍሴ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ
ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ
ድንጋዩን ፡ ሁሉ ፡ እንቅፋቱን
ከፊቴ ፡ ጠርጐ ፡ ተራራውን
በእኔ ፡ ችሎ ፡ የማልችለውን
አለማምዶኛል ፡ ተዐምራቱን
ማቆም ፡ ይችላል ፡ ማዕበሉን
ማዘዝ ፡ ይችላል ፡ ንፋሳቱን
ባያቆመውም ፡ አውራቂሱን
እሻገራለሁ ፡ ይዤ ፡ ቃሉን
ቁዘማውን ፡ ይውሰደው
እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው
ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ
አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ
የሚሆንለት ፡ እርሱ ፡ እንዳለው
የሚቆምለት ፡ እንዳሰበው
የዕድሜህን ፡ ቁጥር ፡ የሚያሰላው
የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ የእኔም ፡ ነው
ስለዚህ ፡ ለምን ፡ ሽንፈትን ፡ ላውራ
ለትንሽ ፡ ነገር ፡ እንደተጠራ
ልታመን ፡ እንጂ ፡ ኃይል ፡ ባለው
ስሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ በተባለው
ቁዘማውን ፡ ይውሰደው
እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው
ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ
ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ
አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ
ኦሮምኛ
አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ
ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ
እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ
እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя