Kishore Kumar Hits

Addisalem Assefa - Alwerdem текст песни

Исполнитель: Addisalem Assefa

альбом: Yamelete Ene Negne


አስገረመኝ አስደነቀኝ ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አረገና
አፌን ፡ ሞላው ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ በምሥጋና
በዝማሬ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ ቤቱ
ሥራዬ ፡ ተሰርቷልና ፡ በምረቱ
ኃይሌን ፡ አድሶት ፡ ጌታዬ ፡ ወጥቻለሁ ፡ አሃሃ ፡ ነቅቻለሁ
ከዚያ ፡ ላይ ፡ ማን ፡ ያወርደኛል ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ አሃሃ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ
ጠላቴ ፡ አታገኘኝም ፡ በትላንቱ ፡ በትላንቱ
ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ አውጥቶኛል ፡ በሰዓቱ ፡ በሰዓቱ
በሰዓቱ ፡ በሰዓቱ (፬x)
የማታ ፡ ለቅሶዬ ፡ ጠዋት ፡ ተለውጦ
እንደ ፡ መርደኪዮስ ፡ ታሪክ ፡ ነገር ፡ ተገልብጦ
በኮረብታ ፡ ሆኜ ፡ መዝሙር ፡ ዘምራለሁ ፡ ሆ
እኔ ፡ ከላይ ፡ ሆኜ ፡ ጠላቴን ፡ ረግጫለሁ
አልወርድም ፡ ከከፍታዬ ፡ ላይ
እግዚአብሔር ፡ አርጐኛል ፡ የበላይ
ዝቅታው ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ ጥሎሃል ፡ ከፊቴ
እግዚአብሔር ፡ ቀኑን ፡ እስኪሰጥ ፡ ድረስ
አይኔ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ እምባን ፡ ቢያፈስ
እንዳለቀስኩኝ ፡ መቼ ፡ ቀረሁኝ
የምስቅበት ፡ ዘመን ፡ መጣልኝ
አፌን ፡ ምሥጋና ፡ ኦሆ ፡ ይኸው ፡ ሞላኝ
አልወርድም ፡ ከከፍታዬ ፡ ላይ
እግዚአብሔር ፡ አርጐኛል ፡ የበላይ
ዝቅታው ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ ጥሎሃል ፡ ከፊቴ
የእግዚአብሔር ፡ ጉልበት ፡ የክንዱ ፡ ብርታት
ይህንን ፡ አድርጓል ፡ ሰርቶ ፡ ታምራት
ክፉ ፡ በሆኑት ፡ ቀናቶች ፡ ፈንታ
ደስታ ፡ አጠገበኝ ፡ ኤልሻዳዩ ፡ ጌታ
አመልከዋለሁ ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ኃይሌን ፡ አድሶት ፡ ጌታዬ ፡ ወጥቻለሁ ፡ አሃሃ ፡ ነቅቻለሁ
ከዚያ ፡ ላይ ፡ ማን ፡ ያወርደኛል ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ አሃሃ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ
ጠላቴ ፡ አታገኘኝም ፡ በትላንቱ ፡ ኦሆሆ ፡ በትላንቱ
ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ አውጥቶኛል ፡ በሰዓቱ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰዓቱ
በሰዓቱ ፡ በሰዓቱ
ልቤን ፡ አልጥልም ፡ ከጠፉት ፡ አህዮች ፡ ላይ
እግዚአብሔር ፡ መጥቷል ፡ ሊሰጠኝ ፡ ከዚያ ፡ በላይ
ሃሳቡ ፡ ለእኔ ፡ ምንጊዜም ፡ የመልካም ፡ ነው
ታምር ፡ ሲሰራ ፡ በሕይወቴ ፡ አይቻለሁ
አልወርድም ፡ ከከፍታዬ ፡ ላይ
እግዚአብሔር ፡ አርጐኛል ፡ የበላይ
ዝቅታው ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ጠላቴ
እግዚአብሔር ፡ ጥሎሃል ፡ ከፊቴ

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители