Kishore Kumar Hits

Yosef kassa - Ayayizen текст песни

Исполнитель: Yosef kassa

альбом: Zmtaw


አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን
እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን
አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን
እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን
ቃየን ፡ ወንድሙን ፡ ገደል
ጌታ ፡ መስዋዕቱን ፡ ስላልተቀበለ
ልቡ ፡ በቅናት ፡ ተሞልቶ
ለጥፋት ፡ ተነሳ ፡ ጭካኔ ፡ ተሞልቶ
ዛሬም ፡ እንደ ፡ ቃየን ፡ አለ ፡ እንደገና
ለምን ፡ ተሳካለት ፡ ብሎ ፡ የሚቀና
ሰይፍ ፡ ይዟል ፡ በእጁ ፡ አፉ ፡ እንደማር
ጉድጓድ ፡ ይቆፍራል ፡ ገድሎ ፡ ሊቀብር
አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን
እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን
ከሁሉ ፡ መጀመሪያ ፡ የታዘዝኩት ፡ ፈቃድ
እንኳን ፡ ወንድሚንና ፡ ጠላቴን ፡ እንድወድ
እጃችን ፡ ተያይዞ ፡ ልባችን ፡ ተራራቀ
ከየት ፡ ፈውስ ፡ ይመጣል ፡ መርዙ ፡ ከተደበቅ
አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን
እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን
በቤትህ ፡ ውድድሩ ፡ በዛ
እኔ ፡ ልታይ ፡ ልታይ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ልግዛ
ቃልህን ፡ የሚሰብከው ፡ ሞልቶ
እንደሚናገረው ፡ ይሚኖረው ፡ ጠፍቶ
ነብይ ፡ አስተማሪ ፡ ሁሉ ፡ ጐራ ፡ ይዞ
ሰይፍ ፡ ይማዘዛል ፡ እዛ ፡ እዚህ ፡ ማዶ
አካል ፡ ተበታትኖ ፡ ዓይኖረውም ፡ ውበት
ማን ፡ ክብርህን ፡ ወስዶ ፡ ይኖራል ፡ በሕይወት
አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን
እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን
ከሁሉ ፡ መጀመሪያ ፡ የታዘዝኩት ፡ ፈቃድ
እንኳን ፡ ወንድሚንና ፡ ጠላቴን ፡ እንድወድ
እጃችን ፡ ተያይዞ ፡ ልባችን ፡ ተራራቀ
ከየት ፡ ፈውስ ፡ ይመጣል ፡ መርዙ ፡ ከተደበቅ
የህግ ፡ ሁሉ ፡ ፍጻሜ ፡ የትዛዛትም ፡ ሁሉ ፡ መጀመሪያ
ባልንጀራህን ፡ እንደ ፡ እራስህ ፡ አድርገህ ፡ ውደድ ፡ ብለኸን
የቤትህ ፡ ማገርና ፡ መሰሶ ፡ የሆነውን ፡ ፍቅርን ፡ ጥለን
ፍቅርን ፡ ስንገፋት ፡ ስትወጣ ፡ ከቤቷ
እግሯን ፡ ተከትሎ ፡ ገባ ፡ ያ ፡ ጠላቷ
ማናከስ ፡ ጀመረ ፡ እንድንጠፋፋ
አደባባይ ፡ ወጥተን ፡ እንድንገፋፋ
ሰው ፡ አካሉን ፡ መብላት ፡ መንከስ ፡ ከጀመረ
መገመት ፡ ይቻላል ፡ ምን ፡ ሊሆን ፡ እንዳለ
አወይ ፡ ጉድ ፡ ሆነናል ፡ ወገን ፡ ተው ፡ እንንቃ
ፍቅር ፡ በሊለበት ፡ እርሱም ፡ የለም ፡ ለካ
አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን
እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители