የልቤን ፡ ማዋየው ፡ የውስጤን ፡ ሚስጥረኛዬ
ባዝንም ፡ ብከፋም ፡ ማይለየኝ ፡ መጽናኛዬ
ነፍሴ ፡ ትረካለች ፡ በአንደበቱ ፡ ቃል ፡ በምክሩ
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ
ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ
የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ
ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ
የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ
እጄን ፡ አነሳሁ ፡ ወደ ፡ ላይ
ወደ ፡ ሚሰማኝ ፡ ወደሚያይ
ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል
እንባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ ያብሳል
አባበዬ ፡ አባትዬ ፡ አባብዬ
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይቀርበኛል ፡ አይርቀኝም
የፍቅር ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ ገብቶልኛል ፡ አይተወኝም
እንዳወራው ፡ ድፍረት ፡ ይሰጠኛል ፡ የፍቅር ፡ ዓይኖቹ
ልቤ ፡ ተፈወሰ ፡ ሲዳስሰኝ ፡ በመልካም ፡ እጆቹ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ
የልቤን ፡ ማዋየው ፡ የውስጤን ፡ ሚስጥረኛዬ
ባዝንም ፡ ብከፋም ፡ ማይለየኝ ፡ መጽናኛዬ
ነፍሴ ፡ ትረካለች ፡ በአንደበቱ ፡ ቃል ፡ በምክሩ
የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ
ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ
የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ
ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ
የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ
እጄን ፡ አነሳሁ ፡ ወደ ፡ ላይ
ወደ ፡ ሚሰማኝ ፡ ወደሚያይ
ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል
እንባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ ያብሳል
አባበዬ ፡ አባትዬ ፡ አባብዬ
ትዋሽ ፡ ዘንድ ፡ እንደሰው ፡ አይደለህ ፡ እውነተኛ ፡ ነህ
የተናገርከውን ፡ ታደርጋለህ ፡ ትፈጽማለህ
ቢታመኑህ ፡ ታማኝ ፡ አንተ ፡ በቻ ፡ ወረት ፡ የሌለህ
ከአጠገቤ ፡ ሁሌ ፡ ማትለየኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ
መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ
ትልቅነትህ ፡ እየገረመኝ
አጠገቤ ፡ ነህ ፡ ይሄም ፡ ሲደንቀኝ
ዘልቀህ ፡ ውስጤ ፡ ገብተሃል
መኖሪያህን ፡ አድርገሃል
የእኔ ፡ ሆነሃል
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя