አዝ ፦ የወደደህ ፡ ልቤ ፡ በእኔ ፡ ማንነቴ
ድንቅ ፡ ድንቅ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ሁሌ ፡ በሕይወቴ
በአንተ ፡ ተይዣለሁ ፡ ማነው ፡ የሚወስደኝ
ፍቅርህ ፡ እኔን ፡ ስቦኛል ፡ አልሰጋም ፡ ተመችተኽኛል (፪x)
አቤቱ ፡ ከልቤ ፡ ላመስግንህ ፡ አንተን
ምሥጋናን ፡ ዝማሬ ፡ ማታ ፡ ቢሆን ፡ በቀን
እሰዋልሃለሁ ፡ የእውነቴን ፡ ሆኜ
ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ፍቅር ፡ አላየሁም ፡ እኔ (፪x)
ለእኔ ፡ ሚሆነኝ ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ
የለኝም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መመኪያ
በአንተ ፡ ሕይወትን ፡ እኔ ፡ አግኝቻለሁ
ኢየሱስ ፡ ለአንተ ፡ እዘምራለሁ
ያለምንም ፡ እኔን ፡ የወደደ
ፍቅር ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የት ፡ አለ
ለሰው ፡ የሚያዝን ፡ የሚራራ
ኧረ ፡ እንደኢየሱስ ፡ የለም ፡ ሌላ
ታዲያ ፡ ለኢየሱስ ፡ ቢዘመር
የእርሱ ፡ ታላቅነት ፡ ቢነገር
እርሱ ፡ ከወደደው ፡ ይሄ ፡ ሁሉ
እዘምራለሁኝ ፡ በየቀኑ
አዝ ፦ የወደደህ ፡ ልቤ ፡ በእኔ ፡ ማንነቴ
ድንቅ ፡ ድንቅ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ሁሌ ፡ በሕይወቴ
በአንተ ፡ ተይዣለሁ ፡ ማነው ፡ የሚወስደኝ
ፍቅርህ ፡ እኔን ፡ ስቦኛል ፡ አልሰጋም ፡ ተመችተኽኛል (፪x)
አቤቱ ፡ ከልቤ ፡ ላመስግንህ ፡ አንተን
ምሥጋናን ፡ ዝማሬ ፡ ማታ ፡ ቢሆን ፡ በቀን
እሰዋልሃለሁ ፡ የእውነቴን ፡ ሆኜ
ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ፍቅር ፡ አላየሁም ፡ እኔ (፪x)
የእውነት ፡ የማይጠፋ ፡ ፍቅር ፡ ያለህ
እንደአንተ ፡ እንደጌታዬ ፡ የት ፡ አለ
እንደሰው ፡ የማትለዋወጥብኝ
አንተ ፡ ነህ ፡ ከጐኔ ፡ ለእኔ ፡ ያለኽኝ
ያለምንም ፡ እኔን ፡ የወደደ
ፍቅር ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የት ፡ አለ
ለሰው ፡ የሚያዝን ፡ የሚራራ
ኧረ ፡ እንደኢየሱስ ፡ የለም ፡ ሌላ
ታዲያ ፡ ለኢየሱስ ፡ ቢዘመር
የእርሱ ፡ ታላቅነት ፡ ቢነገር
እርሱ ፡ ከወደደው ፡ ይሄ ፡ ሁሉ
እዘምራለሁኝ ፡ በየቀኑ (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя