ያን ፡ ያረክልኝ ፡ የማልረሳው
ለእኔ ፡ ብለህ ፡ ነው ፡ ሞቴን ፡ የሞትከው
ለሕይወቴ ፡ ቤዛ ፡ ባትሆን ፡ ኖሮ
የት ፡ እገኝ ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ ድሮ (አዬ ፡ ያኔ ፡ ድሮ)
ሁሌ ፡ ይህን ፡ ሳስብ ፡ የሚደንቀኝ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ ያዋልክልኝ
ያኔ ፡ በሰራኸው ፡ ታላቅ ፡ ስራ
ሕይወትን ፡ አገኘሁ ፡ እንደገና (አዬ ፡ እንደገና)
አዝ ፦ ለዚህ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ምዘምረው
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
ገና ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ አመልካለሁ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
እኔስ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ የአንተ ፡ በመሆኔ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
ከምንም ፡ በላይ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሆኖ ፡ ማነው ፡ የከሰረ
አንተን ፡ ተጠግቶ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አፈረ
ለቀረቡት ፡ ሁሉ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግ
እስቲ ፡ እንደኢየሱስ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ደግ (፪x)
እናት ፡ እንኳን ፡ ልጇን ፡ ብትረሳው
የነበራት ፡ መውደዷ ፡ ቢረሳት
አንተ ፡ አትለወጥ ፡ እንደሰዉ
የአንተ ፡ የዘለዓለም ፡ ፍቅር ፡ ነዉ (አዬ ፡ ፍቅር ፡ ነው)
ሁልጊዜ ፡ አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ታበረታኛለህ ፡ እንዳልፈራ
ከእናት ፡ አባት ፡ በላይ ፡ የሆንከኝ
በአንተ ፡ ተደግፌ ፡ አረፍኩኝ (አዬ ፡ አረፍኩኝ)
አዝ ፦ ለዚህ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ ምዘምረው
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
ገና ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ አመልካለሁ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
እኔስ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ የአንተ ፡ በመሆኔ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
ከምንም ፡ በላይ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
ሁሌ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሰለሌለ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሆኖ ፡ ማነው ፡ የከሰረ
አንተን ፡ ተጠግቶ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አፈረ
ለቀረቡት ፡ ሁሉ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግ
እስቲ ፡ እንደኢየሱስ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ደግ (፪x)
ልክ ፡ እንደ ፡ ጌታዬ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ደግ
ሕይወቱን ፡ የሰጠኝ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ደግ
ወድሃለሁ ፡ ብሎ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ደግ
ልጁ ፡ ያደረገኝ ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ደግ (፫x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя