Kishore Kumar Hits

Yosef kassa - Yihewina Libe текст песни

Исполнитель: Yosef kassa

альбом: Kidan Alegn


ልቤን ፡ ይኽው ፡ እያት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መልሳት
ልቤን ፡ ይኸው ፡ እያት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ አድርጋት
በሰው ፡ ልብ ፡ ብዙ ፡ ሃሳብ ፡ ምኞት ፡ ይገኛል
ዘወትር ፡ ከራሱ ፡ ጋር ፡ ሁሌ ፡ ያወራል
አንደኛው ፡ ስለምድር ፡ ሁሌ ፡ ያስባል
ያ ፡ ደግሞ ፡ ሰማያዊውን ፡ ይናፍቃል
ይህ ፡ ልቤ ፡ የሚመኘው ፡ አንተን ፡ ካልሆነ
መኖሩ ፡ ትርጉም ፡ የለው ፡ ያው ፡ ከንቱ ፡ ሆነ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ በአንተ ፡ ይሞላ ፡ አንተን ፡ ይናፍቅ ፡ አንተን ፡ ይጠማ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ የእኔ ፡ አትሁን ፡ የአንተ ፡ አድርጋት ፡ ውሰዳትና
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ እባክህ ፡ ልጄ ፡ ልብህን ፡ ስጠኝ ፡ ብለሃልና
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ እስቲ ፡ ልወጣት ፡ የአንተን ፡ ዐይነት ፡??? ፡ አድርገህ ፡ ቃኛት
(ይሄውና ፡ ልቤ)
ዘምሮ ፡ አጨብጭቦ ፡ ዘሎ ፡ ይወጣና
ያለቅሳል ፡ እንደገና ፡ ቤቱ ፡ ይገባና
በምድር ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ ልብ ፡ የሚጐዱ
መሽገው ፡ በጨለማ ፡ የሚናደፉ
ጠብቃት ፡ እቺ ፡ ልቤ ፡ እንዳትጐዳ
አበርታኝ ፡ ልቤ ፡ ሁልጊዜ ፡ በአንተ ፡ ትጽና
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ በምድር ፡ አሉ ፡ ከጐኔ ፡ ሆነው ፡ ልብ ፡ የሚገድሉ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ሊያሳዝኗት ፡ ልቤን ፡ ለመጣል ፡ የሚማማሉ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ እኔ ፡ ከያዝኳት ፡ በትንሽ ፡ ነገር ፡ ትሸነፋለች
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ አንተ ፡ ከያዝካት ፡ ሁልጊዜ ፡ ደስታ
(ይሄውና ፡ ልቤ)
ልቤን ፡ ይኽው ፡ እያት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መልሳት
ልቤን ፡ ይኸው ፡ እያት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ አድርጋት
አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ገዢዬ ፡ ብዬ
ግን ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ በልቤ ፡ ላይ ፡ አዝዬ
ወንድሜን ፡ አብሮኝ ፡ ያለውን ፡ እየጠላ
ቂም ፡ ይዞ ፡ ሲጸልይ ፡ ሲዘምር ፡ አይፈራ
ይህ ፡ ልቤ ፡ ይቅርታን ፡ ማድረግ ፡ ካላወቀ
ከአንተ ፡ የሚያገኘው ፡ ምህረት ፡ አለቀ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ማይገባውን ፡ አስቀመጠና ፡ ይሄው ፡ ተበላሸ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ በሰው ፡ እያዘነ ፡ ውስጡን ፡ ውስጡን ፡ ግን ፡ ልቤ ፡ ቆሸሸ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ እስቲ ፡ ለውጠው ፡ ይህ ፡ ካልሆነ ፡ እጐዳለሁና
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ንጹህ ፡ ልብ ፡ ስጠኝ ፡ አንተን ፡ ለማየት ፡ አልችልምና
(ይሄውና ፡ ልቤ)
ወጣሁኝ ፡ ተሳካልኝ ፡ ሆነልኝ ፡ ብዬ
ሌት ፡ ተቀን ፡ ሳመሰግን ፡ በዝቶ ፡ ደስታዬ
የእኔን ፡ መውደቅና ፡ ሃዘን ፡ የሚመኝ
ይመጣል ፡ ከወጣሁበት ፡ ሊያወርደኝ
ይህ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አምኖ ፡ ካልጠነከረ
ይረታል ፡ መጨረሻው ፡ ያው ፡ ተሰበረ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ የእኔን ፡ መሳካት ፡ መከናወኔን ፡ ክፉ ፡ ሲሰማ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ብዙ ፡ ይተጋል ፡ ከአንተ ፡ ሊለየኝ ፡ ልቤን ፡ ሊያደማ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ካልጠነከረ ፡ የአንተ ፡ ለመሆን ፡ ካላመረረ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ቶሎ ፡ ይረታል ፡ በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ካልተቃጠለ
(ይሄውና ፡ ልቤ)
አንዳንዴ ፡ ይሄ ፡ ልቤ ፡ ይጠራጠራል
ስትዘገይ ፡ የማትሰማውም ፡ ይመስለዋል
ነገሮች ፡ ብዙ ፡ በላዩ ፡ ሲከብዱበት
ሲያዝን ፡ የተናገርከው ፡ ሲጠፉበት
ለሚያልፍ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ለማይቆየዉ
ሲሸነፍ ፡ ይሄውልህ ፡ ጌታ ፡ እየዉ
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ በፍፁም ፡ ልብህ ፡ ታመን ፡ ያልከው ፡ እረሳሁና
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ተጠራጠረ ፡ የማያልፍ ፡ መስሎት ፡ ደነበረና
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ኧረ ፡ ፈውሰው ፡ ከሃሳብህ ፡ ጋር ፡ እስኪ ፡ አስማማው
(ይሄውና ፡ ልቤ) ፡ ይኸው ፡ ለውጠው ፡ ልብህን ፡ ክደህ ፡??? ፡ እጠበው
(ይሄውና ፡ ልቤ)
ልቤን ፡ ይኽው ፡ እያት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ መልሳት

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители