Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Yeredal текст песни

Исполнитель: Daniel Amdemichael

альбом: Anbesa

አዝ፦ ይረዳል ፡ ይደግፋል ፡ ጉልበት ፡ ይሆናል ፡ ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ ደራሽ ፡ ለምስኪኖች ፡ አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)
በምድር ፡ ላይ ፡ ለተገፋው ፡ አስታዋሽም ፡ ለሌለው
ሩህሩህ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ መጠጊያማ ፡ ይሆናል
የሃዘን ፡ ማቅን ፡ ቀዶ ፡ እንባንም ፡ ከዓይን ፡ አብሶ
ታሪክን ፡ ይለውጣል ፡ ዳግም ፡ በክብር ፡ ያቆማል
አዝ፦ ይረዳል ፡ ይደግፋል ፡ ጉልበት ፡ ይሆናል ፡ ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ ደራሽ ፡ ለምስኪኖች ፡ አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)
ሰብሳቢ ፡ ነው ፡ እረኛ ፡ ለሆነው ፡ መጻተኛ
ሁሉንም ፡ እንደየአመሉ ፡ በእቅፉ ፡ ይይዛል
አይቶ ፡ መች ፡ ያስችለዋል ፡ ተጠግቶም ፡ ይረዳል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ ቸር ፡ ወዳጅ ፡ እረ ፡ ከየት ፡ ይገኛል
አዝ፦ ይረዳል ፡ ይደግፋል ፡ ጉልበት ፡ ይሆናል ፡ ጌታ (ኦሆሆ)
አይዞህ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ ደራሽ ፡ ለምስኪኖች ፡ አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)
ትልቅ ፡ ነው ፡ ትንሽ ፡ አይል ፡ ሁሉንም ፡ በአንድ ፡ ይወዳል
ፍቅር ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ መቼ ፡ ሰውን ፡ ይለያል
እርዳታውን ፡ ፈልጐ ፡ እርሱን ፡ ለተማጸነው
ታማኝ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የሚያጽናና ፡ መልስ ፡ አለው
አይዞህ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ ደራሽ ፡ ለምስኪኖች ፡ አለኝታ (ኦሆሆ) (፪x)
የምድር ፡ ኑሮ ፡ አማሯችሁ ፡ ተስፋ ፡ የቆረጣችሁ
ኑ ፡ ዛሬ ፡ ወደኢየሱስ ፡ ዕረፍት ፡ ይሰጣችኋል
ሕይወትን ፡ ይለውጣል ፡ ተስፋን ፡ ያለመልማል
ምሬትን ፡ አስወግዶ ፡ በምሥጋና ፡ ይሞላል
አይዞህ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ ደራሽ ፡ ለምስኪኖች ፡ አለኝታ (ኦሆሆ) (፫x)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители