የሕይወት ፡ ሚስጥር ፡ ሳይገባቸው ፡ ሲከተሉ ፡ ለእንጀራቸው
አልተስማሙም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ተመለሱ ፡ ወደ ፡ ኋላ
እኔስ ፡ በርቶልኛል ፡ መዳን ፡ ሆኖልኛል
ሕይወት ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ ፡ የለህ ፡ አቻ
አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ
ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ
ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x)
መድኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ የሚመስልህ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ መከታዬ ፡ ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ከለላዬ
ከአንተ ፡ አልለይም ፡ ሌላው ፡ አይሆንልኝም
የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ ፡ ጥሜን ፡ ታረካለህ
አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ
ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ
ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x)
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ተመችቶኛል ፡ ኢየሱሴ ፡ ጉያህ: ሞቆኛል
በፍቅርህ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሳብከኝ ፡ እስከሞት ፡ ድረስ ፡ የወደድከኝ
በቃ ፡ ወስኛለሁ ፡ አንተን ፡ መርጫለሁ
እርስቴ ፡ ነህ ፡ ብያለሁ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ
ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ
ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ሕይወቴን ፡ አብርተሃል ፡ እኔነቴን ፡ ለውጠሃል
አልለይህም ፡ ወድሃለሁ ፡ ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ጨለማ ፡ ነው
ግዛኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ልስገድ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ነፍሴን ፡ የተቤዠህ ፡ አንተው ፡ ትሻሃለኛለህ
አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ
ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ
ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя