Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Chila Atebel текст песни

Исполнитель: Daniel Amdemichael

альбом: Anbesa

አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል
ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ
አያዋጣም ፡ እዚም ፡ እዚያም
መረጋገጥ ፡ እንዲያው ፡ መዋተት
ትርፉ ፡ ሞት ፡ ነው ፡ ተው ፡ ወንድሜ
አያዛልቅ ፡ በኃጢአት ፡ መዋኘት
ወስነህ ፡ ተቀበል ፡ ጌታን ፡ በልብህ
ኃጢአት ፡ አያባብለህ ፡ ጨክነህ ፡ ተወው ፡ ተወው ፡ ይቅርብህ
አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል
ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ
የዓለም ፡ ኑሮ ፡ እሽኮለሌው
እያሳሳቀ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ነው
ይልቅ ፡ ንቃ ፡ ዛሬ ፡ ወስን
ሞት ፡ እንደው ፡ ቀጠሮ ፡ የለው
ለሕይወትህ ፡ ሰላም ፡ አግኝ ፡ እረፍትን
ና ፡ ብሎ ፡ ሲጠራ ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ አትበል ፡ ስጠው ፡ ልብህን
አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል
ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ
ሀብት ፡ ቢሞላ ፡ ቢትረፈረፍ
ለነፍስ ፡ አንድም ፡ ጠብታ ፡ የለው
አንተነትህን ፡ የሚያረካ
ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሁሉም ፡ ዘበት ፡ ነው
እረኝነቱ ፡ ሥር ፡ መጥተህ ፡ ተጠለል
ኢየሱስን ፡ ምረጠው ፡ ለነፍስ ፡ ለሥጋህ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አትበል
አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል
ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ
ና ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ጌታ ፡ ይፈታል
አንተነትህን ፡ ይለውጣል
በአዲስ ፡ ሕይወት ፡ በአዲስ ፡ ኑሮ
ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሞላል
ሰላምህ ፡ እንደ ፡ ወንዝ ፡ ሞልቶ ፡ ይፈሳል
ዋጋ ፡ አትከፍልበትም ፡ ወስን ፡ ወንድሜ ፡ ጌታ ፡ ይሻላል
አዝ፦ ኧረ ፡ ተው ፡ ወንድሜ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበል
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተል
ኧረ ፡ ተይ ፡ እህቴ ፡ ችላ ፡ ችላ ፡ አትበይ
ሕይወት ፡ ቀልድ ፡ አይደለም ፡ ይብቃ ፡ ዝላዩ ፡ ጌታን ፡ ተከተይ (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители