ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው
ከእንግዲህ ምንስ ያሻኛል
በምድር ከሚታየው ሀብት ይልቅ
የአምላኬ ፍቅር ማርኮኛል
የምድር ዝና ከበሬታ
አላፊ ነው ትቼዋለሁ
የአምላኬ ክብር ባለበት
የኔስ ሐገር በሰማይ ነው
እኔስ ባደባባዮቹ መዋል ማደር ይሻለኛል
የአምላኬ ክብር ሲገለጥ ውስጤን ልቤን ያረካኛል
የእየሱስ ፍቅር ብርቱ ነው ዘወትር አይለወጥም
በቸርነቱ ይዞኛል ከቤቱ የትም አልሄድም
ደስታዬ በጌታ ሙሉ ነው
ከእንግዲህ ምንስ ያሻኛል
በምድር ከሚታየው ሀብት ይልቅ
የአምላኬ ፍቅር ማርኮኛል
የምድር ዝና ከበሬታ
አላፊ ነው ትቼዋለሁ
የአምላኬ ክብር ባለበት
የኔስ ሐገር በሰማይ ነው
ለኔስ ማረፊያዬ ጌታ
የዘላለም መኖሪያዬ
ክብሩን አይቼ ጠግባለው
ሞገሱ ፈሷል በላዬ
ከእርሱ ጋር መሆን መርጣለሁ
የእሱ ክብር በሞላበት
መኖሪያዬ አድርጎታል
እግዚአብሄር በሚገኝበት
ለኔስ ማረፊያዬ ጌታ
የዘላለም መኖሪያዬ
ክብሩን አይቼ ጠግባለው
ሞገሱ ፈሷል በላዬ
ከእርሱ ጋር መሆን መርጣለሁ
የእሱ ክብር በሞላበት
መኖሪያዬ አድርጎታል
እግዚአብሄር በሚገኝበት
ለኔስ ማረፊያዬ ጌታ
የዘላለም መኖሪያዬ
ክብሩን አይቼ ጠግባለው
ሞገሱ ፈሷል በላዬ
ከእርሱ ጋር መሆን መርጣለሁ
የእሱ ክብር በሞላበት
መኖሪያዬ አድርጎታል
እግዚአብሄር በሚገኝበት
እግዚአብሄር በሚገኝበት
እግዚአብሄር በሚገኝበት
ሁሉን ቻይ በሚገኝበት
ሁሉን ቻይ በሚገኝበት
አዳኜ በሚገኝበት
አዳኜ በሚገኝበት
ተስፋዬ በሚገኝበት
ተስፋዬ በሚገኝበትተስፋዬ በሚገኝበት
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя