Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - ልመለስ текст песни

Исполнитель: Daniel Amdemichael

альбом: ባንተ ብርታት


ባባቴ ቤት ሁሉ ሞልቶ
ተትረፍርፎ ኧረ ምን ጠፍቶ
ከሱ ላይ አይኔ ተነሳ
ላይጠቅመው ሌላውን አይቶ
የእራሴ መንገድ አጠፋኝ ተጎዳሁኝ
ሆ ከርያ ለመዋል ተገደድኩኝ
ዛሬ ፍቅሩን ናፍቄያለሁ እመለሳለሁ
ሆ እንደልጅ ባልሆን ባሪያ ሆናለው
አዝ፦ ያለሱማ ኑሮ እንደማይሆን ተረዳሁ
አሁን ይብቃኝ ምንም ላላተርፍ ተጎዳሁ
ልመለስ የቀድሞ ቤቴ ይሻለኛል
ሆ ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይመቸኛል
የዓለም ኑሮ አንገፍግፎኛል ብዙ አራቅቶኛል
ሆ ቸሩ አባቴ እርሱ ይሻለኛል
መስሎኝ ነበር የተጠቀምኩ
ድርሻዬን ይዤ ኮበለልኩ
ሀብቴን በሜዳ በተንኩኝ
አይ ሞኙ መች አስተዋልኩኝ
ያባቴን ምክር ሳልሰማ በመቅረቴ
ሆ ረሃብ ጎዳኝ ተጣብቆ አንጀቴ
ልመለስ ፊቱን ለማየት ብዙም ባልደፍርም
ሆ እንደ እግዚአብሔር ከቶ አይገኝም
ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው
ሰው ድጋፍ አይሆን ሸምበቆ ነው
ልጅነቴ አታለለኝ
አርቆ አለማሰቤ ጎዳኝ
ዛሬስ የእግዚአብሔርን ምህረት ናፍቄያለሁ
ሆ አይጨክንም ይኸን አውቃለሁ
ጉስቁልናዬንም አይቶ ያዝንልኛል
ሆ ውዱ አባቴ ይቅር ይለኛል
አዝ፦ ያለሱማ ኑሮ እንደማይሆን ተረዳሁ
አሁን ይብቃኝ ምንም ላላተርፍ ተጎዳሁ
ልመለስ የቀድሞ ቤቴ ይሻለኛል
ሆ ከኢየሱስ ጋር ኑሮ ይመቸኛል
የዓለም ኑሮ አንገፍግፎኛል ብዙ አራቅቶኛል
ሆ ቸሩ አባቴ እርሱ ይሻለኛል
መድኔ ጋር እመለሳለው
ሀዘኔን በዚያ ረሳለው
ጉስቁልናዬም ይቀራል
እግዚአብሔር ለኔ ይራራል
ያደፈ ልብሴን አውልቆ ሌላ ያለብሰኛል
ሆ ጌታ ፍቅሩን ይመግበኛል
መንፈሱን ያፈስልኛል እፅናናለው
ሆ ለዘላለም በርሱ አርፋለው

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители