Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - በድል ላይ ድልን ይዞ текст песни

Исполнитель: Daniel Amdemichael

альбом: ባንተ ብርታት


በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ
ሥሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው
እንደ ፀሓይ ያበራል ማነው የሚመስለው
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ዓለም ሁሉ ይወቀው
በሰማይ በምድር ፈቺ አልተገኝለትም
ዕንቁ ጌታ ኢየሱስ ነው የሰጠው ማህተም
በረከት ይገባዋል ክብር ይሁን ለንጉሡ
ሥግደትም ይገባዋል ሥግደት ይሁን ለፊቱ
በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ
ሥሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው
እንደ ፀሓይ ያበራል ማነው የሚመስለው
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ዓለም ሁሉ ይወቀው
እልፍ አእላፍ መልኣክቶች ቅኔ ይቀኙለታል
ሽማግሌዎች ፊቱ ወድቀዉ ይሰግዱለታል
በረከት ልትቀበል ይገባሃል ይሉታል
ምስጋና እና ውዳሴ ለእሱ ያቀርቡላታል
በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ
ሥሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው
እንደ ፀሓይ ያበራል ማነው የሚመስለው
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ዓለም ሁሉ ይወቀው
ሀያል ነው ክንደ ብርቱ የሚመስለው የሌለ
በእውነት በፅድቅ የሚፈርድ ዲያብሎስን የጣለ
የዘልአለም ንጉሥ ነው ኢየሱስ የከበረ
በሰማይም በምድርም እጅጉን የገነነ
በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ
ሥሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው
እንደ ፀሓይ ያበራል ማነው የሚመስለው
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ዓለም ሁሉ ይወቀው
በአምባላይ ፈረስን ጌታችን ይቀመጣል
ጠላቱን ያሸንፋል ዓመፀኛውን ይቀጣል
በክብር የተነሳውን በክንዱ ያኖረዋል
የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ለዘልኣለም ይነግሣል
በድል ላይ ድልን ይዞ አሸንፎ የወጣ
ሥሙ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶችም ጌታ ነው
እንደ ፀሓይ ያበራል ማነው የሚመስለው
ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ዓለም ሁሉ ይወቀው

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители