ምህረቱ ገኖ በእኔ ላይ
መልካም የሆነውን ቀን እንዳይ
ጨለማየን ሁሉ አብርቷል
ሐዘን ትካዜ ከኔ ርቋል
አንደበቴን ልክፈት ልናገር
ያረገልኝን ድንቅ ነገር
መልካምነቱ ሁሉ ይስማ
በሱ ዘንድ አይኖርም ጨለማ (2)
እሱ የኔ ወዳጅ
እሱ የኔ እረኛ
ለምን እሰጋለሁ
ለምን ልቤ ይፍራ
እሱ የኔ መሪ
እሱ የኔ እረኛ
ለምን እሰጋለሁ
ለምን ልቤ ይፍራ
አለቴ ነው ጌታየ
ፅኑ ነው መሰረቴ
እኔ ክፋን አልፈራም
ኢየሱስ አለ በህይወቴ (2)
አምላኬ እሱ ነው በኔ ላይ
ልረፍ እንጂ እኔ ምን አሰጋኝ
ብጨነቅ ባወጣው ባወርደው
አንድም የለም የምጨምረው
ታማኝ ነው የኔ እረኛ
የማይደክም ከቶ የማይተኛ
ሐሳቤን በሱ እጥላለሁ
ይረዳኛል አምነዋለሁ (2)
እሱ የኔ ወዳጅ
እሱ የኔ እረኛ
ለምን እሰጋለሁ
ለምን ልቤ ይፍራ
እሱ የኔ መሪ
እሱ የኔ እረኛ
ለምን እሰጋለሁ
ለምን ልቤ ይፍራ
አለቴ ነው ጌታየ
ፅኑ ነው መሰረቴ
እኔ ክፋን አልፈራም
ኢየሱስ አለ በህይወቴ (2)
በልጅነቴ እጁን ይዞ
ትናንትና እንዳሳለፈኝ
ለዛሬም አምላኬ አለልኝ
ለምን ልፍራ ምን አስጨነቀኝ
ምህረቱና ቸርነቱ
ሁሉ ጊዜ ይከተሉኛል
አይተወኝም ለዘልአለም
ኢየሱሴ ቃል ገብቶልኛል ... (2)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя