አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ላውራው
እንዴት ፡ ልተርከው ፡ ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ፡ ውለታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ስጦታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ስንጓዝ ፡ ባሳለፍኳቸው ፡ ዓመታት
ተለይቶኝ ፡ አያውቅም ፡ ለሰከንድ ፡ እንኳን ፡ ለሰዓት
ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ አምላኬ ፡ ለእኔ ፡ ቅርቤ ፡ ነው
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ ታማኝ ፡ ነው
አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ላውራው
እንዴት ፡ ልተርከው ፡ ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ፡ ውለታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ስጦታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ሺህ ፡ ቃላቶች ፡ አይገልፁትም ፡ የጌታዬን ፡ ቸርነት
ምህረቱ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ልክ ፡ የለው ፡ ታማኝነቱ
ጥቂት ፡ አልቆጥብም ፡ ባለኝ ፡ ኃይሌ ፡ እዘምራለሁ
ክብር ፡ የኢየሱስ ፡ ነው ፡ ክብርን ፡ እሰጠዋለሁ
አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ላውራው
እንዴት ፡ ልተርከው ፡ ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ፡ ውለታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ስጦታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ጌታ ፡ አምላኬ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ መኩራሪያ ፡ የምታመንበት
ኢየሱስ ፡ ብዬ ፡ ጠርቼው ፡ ምንጊዜም ፡ የማላፍርበት
ምህረቱን ፡ ልዘምር ፡ ፍቅሩን ፡ ደግሞ ፡ ተዓምራቱን
ሞገሱን ፡ በላዬ ፡ አፍሶታል ፡ በረከቱን
አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ላውራው
እንዴት ፡ ልተርከው ፡ ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ፡ ውለታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
የኢየሱስ ፡ ስጦታው ፡ ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя