አዝ፦ ምህረቱ ፡ እያስደነቀኝ ፡ ለጌታዬ ፡ መዝሙር ፡ ባመጣ
ሊያነቃቃኝ ፡ የአምላኬ ፡ መንፈስ ፡ ሊዳስሰኝ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ወጣ
እዚህ ፡ አይደርስም ፡ ዋጋም ፡ የለውም ፡ በሰዎች ፡ አፍ ፡ የተባለን ፡ ሰው
አይገርምም ፡ ዎይ ፡ በቸርነቱ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ጌታ ፡ ሲያነሳው
አይገርምም ፡ ዎይ (፬x)
አይደንቅም ፡ ዎይ (፬x)
እንደገባኝ ፡ መጠን ፡ እንደተረዳሁት
አምላኬን ፡ ባመልከው ፡ ማነው ፡ ቅር ፡ የሚሰኝ (፪x)
ከልብ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ
ኧረስ ፡ እንደ ፡ ዳዊት ፡ እራቁቴን ፡ ባመልከው
ሜልኮል ፡ አይደለችም ፡ የእኔ ፡ ዳኛ ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)[1]
አዝ፦ ምህረቱ ፡ እያስደነቀኝ ፡ ለጌታዬ ፡ መዝሙር ፡ ባመጣ
ሊያነቃቃኝ ፡ የአምላኬ ፡ መንፈስ ፡ ሊዳስሰኝ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ወጣ
እዚህ ፡ አይደርስም ፡ ዋጋም ፡ የለውም ፡ በሰዎች ፡ አፍ ፡ የተባለን ፡ ሰው
አይገርምም ፡ ዎይ ፡ በቸርነቱ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ጌታ ፡ ሲያነሳው
አይገርምም ፡ ዎይ (፬x)
አይደንቅም ፡ ዎይ (፬x)
እኔ ፡ አውቀው ፡ የለም ፡ ዎይ ፡ ያደረገልኝን
ከጨለማ ፡ አውጥቶ ፡ ቀን ፡ ያወጣልኝን (፪x)
የምን ፡ ቁጠባ ፡ ነው ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ዝምታ
ምሥጋና ፡ ይድረሰው ፡ ለሠራዊት ፡ ጌታ
ለሠራዊት ፡ ጌታ (፪x)
አይገርምም ፡ ዎይ (፬x)
አይደንቅም ፡ ዎይ (፬x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя