ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አንተ ፡ የሁሉ ፡ መድሃኒት
በቸርነት ፡ እየደገፍክ ፡ ታኖረኛለህ ፡ በሕይወት
ምስክር ፡ ነኝ ፡ ለሰራኸው ፡ ብዙ ፡ ተዓምር ፡ አይቼአለሁ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ፍቅርህ ፡ በየዕእለቱ ፡ እደነቃለሁ
አዝ፦ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ምህረት
ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ሥራ
ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)
ቀኑን ፡ ስትጠብቀኝ ፡ ውለህ ፡ ጌታ ፡ ሌሊቱን ፡ አትተኛ
በመውጣቴ ፡ በመግባቴ ፡ ሆነኸኛል ፡ ቸር ፡ እረኛ
መች ፡ ያልቅና ፡ የአንተ ፡ ሥራ ፡ በየዓይነቱ ፡ ብዘረዝር
ቃል ፡ አጣሁ ፡ እጄን ፡ በአፌ ፡ ጭኜ ፡ ከመደነቅ ፡ በቀር
አዝ፦ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ምህረት
ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ ይገርማል ፡ የአንተ ፡ ሥራ
ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ ያኖረኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፣ አቁሞኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋራ (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя