አዝ፦ ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ከእንግዲህ ፡ ምንስ ፡ ያሻኛል
ምድር ፡ ከሚታየው ፡ ሃብት ፡ ይልቅ ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ማርኮኛል
የምድር ፡ ዝና ፡ ከበሬታ ፡ ሃላፊ ፡ ነው ፡ ትቼዋለሁ
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ባለበት ፡ የእኔስ ፡ ሃገር ፡ በሠማይ ፡ ነው
ኦ ፡ ቃሉ ፡ እንደሚናገረው ፡ ሃሌሉያ
እኔስ ፡ በአደባባዮቹ ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ ይሻለኛል
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ሲገለጥ ፡ ውስጤን ፡ ልቤን ፡ ያረካኛል
የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ዘወትር ፡ አይለወጥም
በቸርነቱ ፡ ይዞኛል ፡ ከቤቱ ፡ የትም ፡ አልሄድም
አዝ፦ ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ከእንግዲህ ፡ ምንስ ፡ ያሻኛል
ምድር ፡ ከሚታየው ፡ ሃብት ፡ ይልቅ ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ማርኮኛል
የምድር ፡ ዝና ፡ ከበሬታ ፡ ሃላፊ ፡ ነው ፡ ትቼዋለሁ
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ባለበት ፡ የእኔስ ፡ ሃገር ፡ በሠማይ ፡ ነው
ኦ ፡ ቃሉ ፡ እንደሚናገረው ፡ ሃሌሉያ
ለእኔስ ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ ፡ የዘለዓለም ፡ መኖሪያዬ
ክብሩን ፡ አይቼ ፡ እጠግባለሁ ፡ ሞገስ ፡ ፈሷል ፡ በላዬ
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መሆን ፡ እመርጣለሁ ፡ የእርሱ ፡ ክብር ፡ በሞላበት
መኖሪያዬን ፡ አድርጐታል ፡ እግዚአብሔር ፡ በሚገኝበት
አዝ፦ ደስታዬ ፡ በጌታ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ከእንግዲህ ፡ ምንስ ፡ ያሻኛል
ምድር ፡ ከሚታየው ፡ ሃብት ፡ ይልቅ ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ማርኮኛል
የምድር ፡ ዝና ፡ ከበሬታ ፡ ሃላፊ ፡ ነው ፡ ትቼዋለሁ
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ባለበት ፡ የእኔስ ፡ ሃገር ፡ በሠማይ ፡ ነው
ኦ ፡ ቃሉ ፡ እንደሚናገረው ፡ ሃሌሉያ
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя