Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Yehonegn Tila текст песни

Исполнитель: Daniel Amdemichael

альбом: Yihonal


በምድረ ፡ በዳ ፡ የሆነኝ ፡ ጥላ
ያኔ ፡ የተሸከመኝ ፡ ሆኖኝ ፡ ከለላ (፪x)
ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ የማይለውጠው (፪x)
ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ዛሬም ፡ ጌታ
ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ነገም ፡ ጌታ (፪x)
አዝ፦ ነፍሴ ፡ በጌታ ፡ ሃሴት ፡ አደረገች
በጌታ ፡ ሃሴት ፡ አደረገች
ዛሬም ፡ ብድራቱን ፡ እያሰበች
ብድራቱን ፡ እያሰበች (፪x)
በእርሱ ፡ ቸርነት ፡ አምናን ፡ አልፌ
በበረታው ፡ ክንድ ፡ ላይ ፡ ተደግፌ (፪x)
ዛሬ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ እዘምራለሁ
የሠማይን ፡ አምላክ ፡ አመልከዋለሁ (፪x)
ሃዘኔ ፡ ጠፍቶ ፡ በደስታ
እዘምራለሁ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ
ሞገስ ፡ ለአምላኬ ፡ ክብር ፡ ይሁን
ልሰዋ ፡ ዜማ ፡ ያማረውን
አዝ፦ ነፍሴ ፡ በጌታ ፡ ሃሴት ፡ አደረገች
በጌታ ፡ ሃሴት ፡ አደረገች
ዛሬም ፡ ብድራቱን ፡ እያሰበች
ብድራቱን ፡ እያሰበች (፪x)
ድል ፡ አስለምዶኛል ፡ ጠላትን ፡ ማሸነፍ
ረግጬው ፡ አልፋለሁ ፡ ሺህ ፡ ጦር ፡ ቢሰለፍ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ፡ ስልጣንን ፡ የሰጠኝ
አሸናፊው ፡ ጌታ ፡ አሸናፊ ፡ ያረገኝ
ዘመን ፡ መጣ ፡ መጣ ፡ የዜማ ፡ ወራቱ
ኢየሱስ ፡ የሚከብርበት ፡ ሲመለክ ፡ በቤቱ
ያማረ ፡ ዝማሬ ፡ ቅኔዉም ፡ ለእርሱ ፡ ነው
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
መደገፊያ ፡ ነው (፪x)
ድል ፡ አስለምዶኛል ፡ ጠላትን ፡ ማሸነፍ
ረግጬው ፡ አልፋለሁ ፡ ሺህ ፡ ጦር ፡ ቢሰለፍ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ ፡ ስልጣንን ፡ የሰጠኝ
አሸናፊው ፡ ጌታ ፡ አሸናፊ ፡ ያረገኝ
ዘመን ፡ መጣ ፡ መጣ ፡ የዜማ ፡ ወራቱ
ኢየሱስ ፡ የሚከብርበት ፡ ሲመለክ ፡ በቤቱ
ያማረ ፡ ዝማሬ ፡ ቅኔዉም ፡ ለእርሱ ፡ ነው
የይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ መታመኛዬ ፡ ነው
መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
መደገፊያ ፡ ነው (፪x)
መታመኛዬ ፡ ነው (፪x)
መደገፊያ ፡ ነው (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители