የተደገፍኩበት ጠንካራ አለት ነው
የተገዛሁበት ደሙ ነው
እግዚአብሔር የረዳው ከሞት የተረፈ
ኧረ እንደኔ ማን ነው ያረፈ
ላመስግነው እንጂ በገናዬን ልቃኝ
ይውጣ ዝማሪዬ ለሆነው የበላይ
አዳነኝ በፍቅሩ መንገዴን ቀየረው
ለጌታ ለኢየሱስ ምስጋናዬ ይኸው
ምህረት በኔ ላይ ጠንክራለችና ጠንክራለችና
ሀይሌ ታድሶልኝ ቆምኩኝ እንደገና ቆምኩኝ እንደገና
የገባኝ ይሄ ነው የዘላለም ፍቅር የዘላለም ፍቅር
ከሞት የታደገኝ አምላኬ ምህረት አምላኬ ምህረት
በፍቅር ደገፍክና በምክር አቆምክና
በኔ ላይ አሳየኸው ምህረትን ገለጥክና
በፍቅር ደገፍክና በምክር አቆምክና
በኔ ላይ አሳየኸው ምህረትን ገለጥክና
የቅኖች ዳኛ ለተጠቃው ፈራጅ
እረዳት ለሌለው ተሟጋች
መድሀኒቴ እሱ ነው ልቤን የጣልኩበት
ኢየሱስ የተደገፍኩበት
አቀናው መንገዴን ምህረት አብዝቶልኝ
ሰላም ገባ ውስጤ መድሀኒት ሆነልኝ
እሱን ለተጠጋ በእውነት ለታመነው
ጌታ እሩቅ አደለም ለጠሩት ቅርብ ነው
ምህረት በኔ ላይ ጠንክራለችና ጠንክራለችና
ሀይሌ ታድሶልኝ ቆምኩኝ እንደገና ቆምኩኝ እንደገና
የገባኝ ይሄ ነው የዘላለም ፍቅር የዘላለም ፍቅር
ከሞት የታደገኝ አምላኬ ምህረት አምላኬ ምህረት
በፍቅር ደገፍክና በምክር አቆምክና
በኔ ላይ አሳየኸው ምህረትን ገለጥክና
በፍቅር ደገፍክና በምክር አቆምክና
በኔ ላይ አሳየኸው ምህረትን ገለጥክና
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя