Kishore Kumar Hits

Daniel Amdemichael - Keberilen текст песни

Исполнитель: Daniel Amdemichael

альбом: Selam Vol. 5


የድሃን ፡ ማድጋ ፡ ዘይት ፡ የሚሞላው
ከችግር ፡ አውጥቶ ፡ በደስታ ፡ ሚያኖረው
ለአንድ ፡ አይደለም ፡ ኢየሱስ ፡ ለብዙ ፡ ይተርፋል
ክበር ፡ እንበለው ፡ ይገባዋል
አዝ: - ክበር ፡ ክበርልን ፡ ክበር ፡ እንበለው
መክበር ፡ የሚገባው ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነው
ለቅሶን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሳቅ ፡ ለውጧል
ኢየሱስ ፡ ሊመሰገን ፡ ይገባዋል
በሽባነት ፡ ታስሮ ፡ እንድሜውን ፡ ለፈጀው
ወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ ትቶት ፡ ተስፋ ፡ ለቆረጠው
ታምረኛው ፡ ኢየሱስ ፡ በጊዜው ፡ ይደርሳል
እስራቱን ፡ ፈቶ ፡ ያዘልላል
አዝ: - ክበር ፡ ክበርልን ፡ ክበር ፡ እንበለው
መክበር ፡ የሚገባው ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነው
ለቅሶን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሳቅ ፡ ለውጧል
ኢየሱስ ፡ ሊመሰገን ፡ ይገባዋል
ሙቱን ፡ ከመቃብር ፡ ተጣርቶ ፡ ያስነሳል
በቃ ፡ የተባለውን ፡ ነፍስ ፡ ይዘራበታል
ለእርሱ ፡ ማይታዘዝ ፡ ምን ፡ አለ ፡ በውኑ
ከፍ ፡ ብሎ ፡ ይንገሥ ፡ በዙፋኑ
አዝ: - ክበር ፡ ክበርልን ፡ ክበር ፡ እንበለው
መክበር ፡ የሚገባው ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነው
ለቅሶን ፡ ወደ ፡ ደስታ ፡ ወደ ፡ ሳቅ ፡ ለውጧል
ኢየሱስ ፡ ሊመሰገን ፡ ይገባዋል

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители