አዝ፦ ይገርመኛል ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ቸርነቱን
አልታክትም ፡ ሁሌ ፡ ባወራው ፡ ምህረቱን
እርሱ ፡ በሰራው ፡ ጸድቅ ፡ እኔን ፡ ያኖረኛል
ስለመዳኔ ፡ ላከብረው ፡ ይገባኛል ፡ ኦሆ
ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ላድርገው ፡ ክብርን ፡ ልስጠው ፡ ኦሆ
በሠማዩ ፡ መዝገብ ፡ ስሜን ፡ ስለጻፈው
ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጸድቄአለሁኝ ፡ በእርሱ ፡ ስራ ፡ ኦሆ
እኖራለሁ ፡ ድንቁን ፡ ታሪኩን ፡ ሳወራ
ኢየሱስ ፡ መድኅኔ ፡ ማረፊያ ፡ ሆኖኛል
ከሞት ፡ ከጨለማ ፡ መንጥቆ ፡ አውጥቶኛል
የከበረ ፡ ስሙን ፡ ዘወትር ፡ እየጠራሁ ፡ ቅኔን ፡ እቀኛለሁ
በታላቅ ፡ ጉባኤ ፡ በልጆቹ ፡ መሃል ፡ አመሰግናለሁ
በልጆቹ ፡ መሃል ፡ አመሰግናለሁ (፫x) ፡ አመሰግናለሁ
ተመስገን ፡ ትላለች ፡ እርሱ ፡ ያዳናት ፡ ነፍሴ
ሳመልከው ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ በእውነት ፡ በመንፈሴ
አድናቆቴም ፡ ይኸው ፡ አክብሮቴም ፡ ይኸው ፡ ፊቱ ፡ ልስገድለት
ለጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ለነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት
ለጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት
ለነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ለጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ ይሁንለት
አዝ፦ ይገርመኛል ፡ የአምላኬ ፡ ፍቅር ፡ ቸርነቱን
አልታክትም ፡ ሁሌ ፡ ባወራው ፡ ምህረቱን
እርሱ ፡ በሰራው ፡ ጸድቅ ፡ እኔን ፡ ያኖረኛል
ስለመዳኔ ፡ ላከብረው ፡ ይገባኛል ፡ ኦሆ
ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ላድርገው ፡ ክብርን ፡ ልስጠው ፡ ኦሆ
በሠማዩ ፡ መዝገብ ፡ ስሜን ፡ ስለጻፈው
ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጸድቄአለሁኝ ፡ በእርሱ ፡ ስራ ፡ ኦሆ
እኖራለሁ ፡ ድንቁን ፡ ታሪኩን ፡ ሳወራ
አምላክ ፡ አባት ፡ ሆነኝ ፡ በወንጌል ፡ አምኜ
በደሙ ፡ ዋጋ ፡ ገዛኝ ፡ እንድኖር ፡ ልጁ ፡ ሆኜ
እንግዲህ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ስለታላቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ መዳኔን ፡ እያሰብኩ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ መዳኔን ፡ እያሰብኩ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя