አዝ፦ ከምንጩ ፡ ስለቀዳሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ
ምህረት ፡ ስላገኘሁ ፡ አቀርባለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
በደሙ ፡ ስለዋጀኝ ፡ ስላዳነኝ ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ
ለኪዳኑ ፡ ስላሰበኝ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጌታዬን ፡ ስባርክ
ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ መድህኔ
ስላዳነኝ ፡ ከሞት ፡ ከኩነኔ
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ የጸዮኑ ፡ አለት
ተቆረጠ ፡ የኀጢአት ፡ ሰንሰለት
ለቤዛ ፡ ቀን ፡ በእርሱ ፡ ታትሜያለሁ
በመንፈሱ ፡ ልደት ፡ አግኝቻለሁ
ሠማያዊ ፡ ዜጋ ፡ የመንግሥቱ
ተመረጥኩኘ ፡ እንድኖር ፡ በእርስቱ
ፀጋ ፡ ሰጠኝ ፡ የዘለላእም ፡ ደህንነት
ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ለተደገፉበት
ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ በየእለቱ
ላገልግለው ፡ በደስታ ፡ በቤቱ
አዝ፦ ከምንጩ ፡ ስለቀዳሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ
ምህረት ፡ ስላገኘሁ ፡ አቀርባለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
በደሙ ፡ ስለዋጀኝ ፡ ስላዳነኝ ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ
ለኪዳኑ ፡ ስላሰበኝ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጌታዬን ፡ ስባርክ
ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ መድህኔ
ስላዳነኝ ፡ ከሞት ፡ ከኩነኔ
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ የጸዮኑ ፡ አለት
ተቆረጠ ፡ የኀጢአት ፡ ሰንሰለት
አምልኮዬ ፡ ለመድሃኒዓለም
ታላቅ ፡ ስሙ ፡ ይመስገን ፡ ዘለዓለም
ለሚገዛው ፡ ሠማይን ፡ ምድርን
አውጃለሁ ፡ ዘምራለሁ ፡ ክብሩን
ለታደገኝ ፡ ለታማኝ ፡ ወዳጄ
ዘምራለሁ ፡ በደስታ ፡ ፈቅጄ
አወራለሁ ፡ ፍቅሩን ፡ ተዐምራቱን
እርሱ ፡ ብቻ ፡ መድሃኒት ፡ መሆኑን
አይገርምም ፡ ወይ ፡ በአምላክ ፡ መታሰቤ
ላገለግል ፡ ለአመልከው ፡ ቀርቤ
የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ አገልጋይ ፡ በቤቱ
ሎሌ ፡ አደረገኝ ፡ ጌታ ፡ በችሎቱ
ኢየሱስ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ በሕይወቴ
እርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ስሬ ፡ መሰረቴ
ጠጥቻለሁ ፡ የዘለዓለም ፡ ውሃ
ለመለመ ፡ የነፍሴ ፡ በረሃ
አዝ፦ ከምንጩ ፡ ስለቀዳሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ
ምህረት ፡ ስላገኘሁ ፡ አቀርባለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ
በደሙ ፡ ስለዋጀኝ ፡ ስላዳነኝ ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ
ለኪዳኑ ፡ ስላሰበኝ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጌታዬን ፡ ስባርክ
ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ መድህኔ
ስላዳነኝ ፡ ከሞት ፡ ከኩነኔ
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ የጸዮኑ ፡ አለት
ተቆረጠ ፡ የኀጢአት ፡ ሰንሰለት
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя