ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)
ከልጅነት ፡ የተሸከመኝ
እስከሽምግልና ፡ የሚመራኝ
አሳዳጊ ፡ ይህ ፡ ወላጅ ፡ የሆነኝ
ያለእርሱ ፡ ወገን ፡ ማነው ፡ ያለኝ
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)
ቢከፋኝ ፡ ቢደላኝ ፡ እርሱ ፡ ነው
ሁልጊዜ ፡ ከጐኔ ፡ ማገኘው
ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ወዳጄ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተቆርቋሪ ፡ ለእኔ
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)
እግሬን ፡ ከጨለማ ፡ መልሷል
በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ ውስጤን ፡ አስሯል
ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ለእኔ
በፍቅሩ ፡ ተማርካለች ፡ ነፍሴ
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)
ሕያው ፡ ነው ፡ ምንም ፡ አያረጅም
ዘመን ፡ ሲያልፍ ፡ እርሱ ፡ አይለወጥም
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነው
ታማኝነቱ ፡ ለእኔ ፡ ብዙ ፡ ነው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ የሰበረው
ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ አላውቅም
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)
በጣም ፡ ተዋደናል ፡ አንለያይም (፪x)
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя