Kishore Kumar Hits

Awtaru Kebede - Egziabhier Sinager текст песни

Исполнитель: Awtaru Kebede

альбом: Yikerta,Vol. 5


እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ሁሉንም ፡ ይችላል ፡ እኔ ፡ ዝም ፡ ልበል
አምላኬ ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ምድር ፡ ዝም ፡ ትበል
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)
ሞቷል ወይ፡ ፡ ቀበርከው ፡ ወይ
ዛሬ ፡ ቀኑ ፡ ነው (፫x) ፡ ክብሩን ፡ ልታይ
ቀኑ ፡ ነው ፡ ክብሩን ፡ ልታይ (፬x)
አረጀ ፡ አብርሃም ፡ ደከመ ፡ ጉልበቱ
ዛሬማ ፡ አይደለም ፡ እንደ ፡ ልጅነቱ
አበቃ ፡ ተቆርጧል ፡ የእርሱ ፡ ነገርማ
ምድር ፡ ተገረመች ፡ መውለዱ ፡ ሲሰማ
ምንም ፡ በሌለበት ፡ ጭር ፡ ባለው ፡ ቦታ
አንድ ብሎ ፡ ጀመረ ፡ ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ጌታ
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)
ብቻ ፡ ይናገረኝ ፡ ቃል ፥ ይዉጣ ፣ ከአፉ
እጠብቀዋለሁ ፡ ቀኑ ፡ ቢሆን ፡ ክፉ
በገናን ፡ አልሰቅልም ፡ እደረድራለሁ
ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አባቴ ፡ ትልቅ ፡ ነው
አባቴ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ሁሉንም ፡ ይችላል ፡ እኔ ፡ ዝም ፡ ልበል
አምላኬ ፡ ሲናገር ፡ ሰማሁ ፡ አንድ ፡ ነገር
ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ምድር ፡ ዝም ፡ ትበል
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)
ሞቷል ፡ ወይ ፡ ቀበርከው ፡ ወይ
ዛሬ ፡ ቀኑ ፡ ነው (፫x) ፡ ክብሩን ፡ ልታይ
ቀኑ ፡ ነው ፡ ክብሩን ፡ ልታይ (፬x)
የማሰሮው ፡ ዘይት ፡ የማድጋው ፡ ዱቄት
አንድ ፡ ቀን ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ነገ ፡ የለም ፡ ሕይወት
እያለች ፡ ተጨንቃ ፡ ከአንድ ፡ ልጇ ፡ ጋራ
እግዚአብሔር ፡ አሰባት ፡ መጣ ፡ የእርሷ ፡ ተራ
ዝናብ ፡ እስኪመጣ ፡ ምድር ፡ እስኪያበቅል
በበረከት ፡ ሞላው ፡ ቤቷን ፡ በሰላም
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቋጠሮዬን ፡ መፍታት
ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ የሞተ ፡ ማስነሳት (፪x)

Поcмотреть все песни артиста

Другие альбомы исполнителя

Похожие исполнители