Jano Band - Zew Zew текст песни
Исполнитель:
Jano Band
альбом: Lerasih New
ከልጅ ካዋቂው መስሎ ጓደኛ
ቀኑን ሳያርፈው ለሊት ሳይተኛ
ካዘነው ሲያዝን ከሳቀው ሲስቅ
እዚህ እያጣላ እዚያ ሲያስታርቅ
ደሞ በሌላ ልቡ እስኪረታ
ይቺን ሲያገባ ያቺን ሲፈታ
ወጣ ገባ ሲል እዚም እዚያም
ቀደመው ጊዜ አንዱን ሳይተወው
እንዲያው ዘው ዘው።
አይ ዘው ዘው ጥርስ የታደለው
አይ ዘው ዘው ስንቱን አሞኘው
አይ ዘው ዘው ስንቱን አቄለው
አይ ዘው ዘው ዛሬ አለፈና
አይ ዘው ዘው ጥርሶቹም አልቀው
አይ ዘው ዘው ሳይወርሰው ሽበት
አይ ዘው ዘው በድዱ ሳቀው
አይ ዘው ዘው።
ቀብሮ በውስጡ ከያዘው እውነት
በልጦ በስሙ ሲምል ሲገዘት
አፈ ቅቤው ሰው አለም ሳትበቃው
ሰማይ ልርገጥ ሲል መሬት እርቃው
በጠላው እውነት ዛሬ ተወርሶ
የሇላው ሲያይ የፈራው ደርሶ
ጊዜ በቁጭት ሲወዘውዘው
ምኑን ይልቀቀው የቱን ይያዘው።
((እንዲያው ዘውዘው))
አይ ዘው ዘው ጥርስ የታደለው
አይ ዘው ዘው ስንቱን አሞኘው
አይ ዘው ዘው ስንቱን አቄለው
አይ ዘው ዘው ዛሬ አለፈና
አይ ዘው ዘው ጥርሶቹም አልቀው
አይ ዘው ዘው ሳይወርሰው ሽበት
አይ ዘው ዘው በድዱ ሳቀው
አይ ዘው ዘው።
የሸሸ ለት ወዳጅ ጥርስ ላይመልሰው
አትሳቅ ለይምሰል እባክህ አንተ ሰው
ሰምቶ ከመናገር በቡና ቤት ወሬ
ትደርሳለህ ተመለስ ተው ስማኝ አጅሬ።
አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ቀድሞ እድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጡስ ምች ሊጥም
አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ቀድሞ እድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጡስ ምች ሊጥም
((እንዲያው ዘው ዘው))
አይ ዘው ዘው ጥርስ የታደለው
አይ ዘው ዘው ስንቱን አሞኘው
አይ ዘው ዘው ስንቱን አቄለው
አይ ዘው ዘው ዛሬ አለፈና
አይ ዘው ዘው ጥርሶቹም አልቀው
አይ ዘው ዘው ሳይወርሰው ሽበት
አይ ዘው ዘው በድዱ ሳቀው
አይ ዘው ዘው።
አይ ዘው ዘው
አይ ዘው ዘው
አይ ዘው ዘው
አይ ዘው ዘው። by yonas nesex
Поcмотреть все песни артиста
Другие альбомы исполнителя